Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 119
  • File Size 2.32 MB
  • File Count 1
  • Create Date May 22, 2024
  • Last Updated May 22, 2024

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ የተከናወነ ክትትል ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የኦሞ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ እና መደበኛ የመፍሰሻ መስመሩን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት በጎርፍ ከተጥለቀለቁ የወንዙ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢዎች በተለይም ከዳሰነች ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ ከጥቅምት 5 እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ክትትል በማከናወን ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ኢሰመኮ የክትትል ሥራውን ሲያከናውን በቡድን ውይይት፣ በቃለ መጠይቅ፣ በሰነድ ምርመራ እና በመጠለያ ጣቢያዎች ላይ የአካል ምልከታ በማድረግ መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን አሰባስቧል፡፡ ከተፈናቃዮች ጋር የጾታ፣ የዕድሜ እና የአካል ጉዳት ሁኔታ ስብጥርን ታሳቢ ያደረጉ 6 የቡድን ውይይቶችን፣ እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው 11 የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከ5 መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ የተራድዖ ድርጅቶች እና ከሲቪል ማኅበራት ተወካዮች ጋር ውይይቶችን እና ቃለ መጠይቆችን አድርጓል። በተጨማሪ የክትትሉን ግኝቶች ለማጋራት፣ በክትትሉ በተለዩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አሳሳቢ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች እና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ለመወያየት እንዲሁም ምክረ ሐሳቦቹ እንዲፈጸሙ ለመወትወት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተለያዩ ጊዜያት የምክክር መድረኮችን አካሂዷል።