የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በውይይቱ ላይ በሰጡት ማብራሪያ፤ አድካሚውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት በመምራት እዚህ ደረጃ ለመድረስ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ላሳዩት ትጋት ምስጋና አቅርበዋል
ኢሰመኮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር ያለውን ትብብርና ቅንጅት አጠናክሮ ይቀጥላል
5ኛው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት (Human Rights Moot Court) ፍጻሜ ውድድር ተካሄደ
ተዋዋይ ሀገራት የማናቸውም ዐይነት የእንክብካቤ እጦት፣ ብዝበዛ፣ ያልተገባ አያያዝ፣ ማሰቃየት ወይም ሌላ ማናቸውም ዐይነት ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ወይም ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ወይም የትጥቅ ግጭት ሰለባ የሆነን ሕፃን በአካልና በሥነ ልቦና ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግምና ከኅብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል ለማድረግ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ
States Parties shall take all appropriate measures to promote physical and psychological recovery and social reintegration of a child victim of any form of neglect, exploitation, or abuse; torture or any other form of cruel, inhuman or degrading treatment or punishment; or armed conflicts
በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻዎች ምክረ ሐሳቦችን በቅንጅት ሊተገብሩ ይገባል
የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ በማረሚያ ቤቶች ላይ የሰብአዊ መብቶች አከባበር እና አጠባበቅ፤ የኑሮ ሁኔታ እንዲሁም ከቀለብ ጋር በተያያዘ በክትትል መምሪያ ዳይሮክተሬት በኩል በየጊዜው ክትትል ያደርጋል። በክትትል ሂደቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚበረታቱ ለውጦች ቢኖሩም ከቀለብ እና ከበጀት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች ትኩረት ሊሰጥባቸው ይገባል ብለዋል
የሰብአዊ መብቶችን ባህል ለማድረግ ተተኪ ትውልድን በሰብአዊ መብቶች ዕውቀትና ክህሎት ማነጽ ይገባል
የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት መብት ለማረጋገጥ የትምህርት ግብአት አቅርቦት፣ ከባቢያዊ እና የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም የአመለካከት ክፍተቶች ላይ መሥራት ያስፈልጋል
ጥገኝነት የመጠየቅ መብት ማለት ምን ማለት ነው? ጥገኝነት የመጠየቅ መብት የሕግ መሠረቶች ምንድን ናቸው? የጥገኝነት ጠያቂዎች መብቶች ምንድን ናቸው? ኢትዮጵያ ውስጥ ጥገኝነት ለማግኘት የት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል? ኢትዮጵያ ውስጥ ጥገኝነት መጠየቅ ምን ሂደትን ያካትታል?