የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ በውይይቱ ተሳትፈዋል
በተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እና አሠራሮችን የማሻሻል ተግባራትን ማጠናከር ያስፈልጋል
የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ እና ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች በቂ ትኩረት በሚሰጥ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ሊያደርጉ ይገባል
ኢሰመኮ የሰዎች እገታ እየተበራከት ነው አለ
ኢሰመኮ በዚህ መግለጫው የእገታ ጉዳዮች ለማሳያነት አቅርቧል
ታጣቂዎች የሚፈጽሟቸው የእገታ ተግባራት ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ጋር የሚቃረን በመሆኑ ከድርጊታቸው መቆጠብ እንደሚኖርባቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል
የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት መብት ለማረጋገጥ የመምህራንን ግንዛቤ በማዳበር የትምህርት አሰጣጡ ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ማስቻል ይገባል
በሁለቱ ክልሎች ከተራዘሙ የትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው የሕግ ማስከበርና የመንግሥት መዋቅር መላላት ምክንያት በሰላማዊ ሰዎች ላይ በታጣቂ ኃይሎች፣ ለዘረፋ በተደራጁ ቡድኖችና በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አባሎች የሚፈጸሙ እገታዎች ተባብሰውና ተስፋፍተው መቀጠላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል ኮሚሽኑ
በአገሪቱ የሕግና ሥርዐት አለመከበርና የመንግሥት ሀገርን አረጋግቶ የመምራት ሂደት አለመቻል ሥርዐት አልበኝነትን እያነገሰ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል
ኢሰመኮ ባወጣው ሪፖርት እገታዎቹው ለዘረፋ "በተደራጁ ቡድኖች እንዲሁም በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት" የሚፈጸሙ ናቸው ብሏል