Daniel Bekele የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዓመታዊ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 5፤ 2015 ይፋ አድርጓል። ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው ሪፖርት ከሰኔ 2014 እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ያሉትን አስራ ሁለት ወራት የሚሸፍን ነው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይህንን የተናገረው ከሰኔ 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ድረስ የነበረውን ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርትን ሀምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው
በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ችግሮቹን የሚመጥን የመፍትሔ እርምጃ እየተወሰደ አይደለም ተብሏል
ኢሰመኮ ቀዳሚው ትኩረት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋነኛ ምክንያት የሆኑ የሥር መንስኤዎችን ለመፍታት ሊሆን እንደሚገባ አሳሰበ
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሥር መንስኤ የሆኑ የተጠያቂነት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት መላላት እና የሰላም እና ደኅንነት እጦት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት የመንግሥት ከፍተኛ እና ያልተቋረጠ ጥረት ያሻል (የ2015 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት)
ስልጠናዎቹ በአካል ጉዳተኞች፣ በሕፃናት፣ እንዲሁም በሕግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው
የሦስትዮሽ ትብብሩ የመብት ተሟጋቾች ሊደርስባቸው የሚችለውን ጫና እና እንግልት በጋራ ለመከላከል እና ለመቋቋም ትልቅ ሚና ይኖረዋል
የፍትሕ አካላትን የበጀት ውስንነት በመቅረፍ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት በቂ ትኩረት ይፈልጋል
በአገር አቀፍ ደረጃ ለግንባታው ኢንዱስትሪ ሕጎች ቢወጡም ተግባራዊ ባለመደረጋቸው፣ የግንባታ ሠራተኞች ለመብት ጥሰትና ለአደጋ እየተዳረጉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በሥራ ዘርፉ የሚንቀሳቀሱ አስፈጻሚ ተቋማትን በማጠናከር፣ ባለድርሻዎችን አቀናጅቶ እና አስተባብሮ የሚመራ ሥርዓት መዘርጋት አለበትም ብሏል ኢሰመኮ