ተፋላሚ ኃይላት የተኩስ አቁም አድርገው ለሰላማዊ መፍትኄ ንግግር እንዲጀምሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አስተላልፏል
በኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶችን የሚያጣራውና በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክርቤት የተቋቋመው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት መርማሪ ኮሚሽን ያገረሸው ጦርነት እንዳሳዘነው ገለጸ
አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች በግጭቱ የደረሰባቸውን ከፍተኛ የመብቶች ጥሰት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል
በርካታ ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየው አሰቃቂ የግድያ ድርጊት መደበኛ እና ኢ-መደበኛ የመንግሥት ኃይሎች ከወራት በፊት የፈጸሙት መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ
Ethiopia's state-appointed human rights commission said in a statement late on Saturday that a video circulating on social media showed government security forces carrying out at least 30 extrajudicial killings in December 2021
ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሰረት የተሟላ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በድጋሚ ያሳስባል
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መረጃ መሠረት እስከ ግንቦት 21 ቀን 2014 ድረስ 19 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል
የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት መብትን የሚመለከት አዋጅ የወጣ እና ሥራ ላይ የዋለ ቢሆንም፤ በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ያለው ያልተጣጣመ አሠራር አካል ጉዳተኞች በሥራ ቅጥር፣ ዕድገት፣ ድልድል፣ ዝውውር፣ ሥልጠናና ሌሎች የሥራ ሁኔታዎች ወቅት መድልዎ እንዲደርስባቸው መንስኤ ነው
የተወሰኑት ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በቤተሰቦቻቸው የተጎበኙና በተለያየ የጊዜ መጠን ወደ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም፤ በርካታ ታሳሪዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ መታሰራቸውን፣ ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውን፣ በቤተሰብ አለመጎብኘታቸውን ተመልክቷል
በጦርነቱ ተሳታፊ በሆኑ ሁሉም ኃይሎች የተፈጸሙ ጥሰቶች ላይ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ የመጀመሪያው ኃላፊነት በመንግሥት ላይ የሚወድቅ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውሷል