የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተፈጻሚነት ጊዜ “ከአንድ ወር ወይም የተወሰኑ ሳምንታት ላልበለጠ ጊዜ ብቻ” እንዲሆን እንዲያደርግ እና የተፈጻሚነት ወሰኑንም በአማራ ክልል ብቻ እንዲገድብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ
በአማራ ክልል፣ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂ መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያጸድቀው ከኾነ፤ ተፈጻሚነቱ ከሳምንታት ወይም ከአንድ ወር እንዳይበልጥ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ
የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በአማራ ክልል በሙሉ እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ እንደአስፈላጊነቱ ተፈጻሚ የሚሆን እና ለስድስት ወራት የሚቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት በአማራ ክልል ብቻ እንዲገደብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ፤ ኮሚሽኑ የአፈጻጸም ጊዜው ወደ አንድ ወር እንዲያጥርም ምክረ ሃሳብ አቅርቧል
በማንኛውም ምክንያት ቢሆን የሚታወጅ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ለሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው። ኢሰመኮ በተለያዩ ወቅቶች በሀገሪቱ በከፊልም ሆነ በሀገር አቀፍ የተጣሉ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች በመቋቋሚያ አዋጁ በተጣለበት ኃላፊነት መሠረት ክትትል እና ምርመራ አድርጎ፣ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና  ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በእነዚህ የክትትል እና የምርመራ ግኝቶቹም መሠረት ከዚህ ቀደም...
ከአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታው ጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት በተጨማሪ የፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ ወቅት ክትትል (Parliamentary Oversight) እና የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል የማድረግ ኃላፊነት ሊረጋገጥ ይገባል
በአማራ ክልል እየተባባሰ የመጣው የትጥቅ ግጭት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እየተባባሰ የመጣውን የትጥቅ ግጭት እና የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጠው ጠይቋል
በአማራ ክልል በመከላከያና በታጣቂ ሚሊሻዎች፣ ፋኖ የተነሳው ግጭት መባባሱን ተከትሎ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
ሁሉም ወገኖች ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፣ የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎች በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ነዋሪዎችን ለበለጠ ጉዳት እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይዳርጉ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ያሳስባል
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅትም ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል