የግሉ የጤና ዘርፍ አገልግሎት ከመንግሥት የጤና ዘርፍ አገልግሎት አንጻር ሲታይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሕብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል
የኢትዮጵያ ስብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣ ነው ባለው እና በመንግስት የጸጥታ ኃይላት የሚፈጸም ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል
የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ እና የመንግሥት አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የግሉ የጤና ዘርፍ ከሕብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም ጋር የተመጣጠነ እና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት አቅርቦት ላይ ያተኮረ ባለ 39 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት ይፋ አድርጓል። የጤና መብት ተገኝነት፣ ተደራሽነት፣ ተቀባይነት እና ጥራት ላይ ያተኮሩ አራት ዋና ዋና ይዘቶች ያሉት ሲሆን ክትትሉ በተደራሽነት (accessibility) ሥር ከተጠቃለሉት ንዑስ ይዘቶች መካከል በገንዘብ ተደራሽነት...

ተማሪዎቹ አገልግሎት በሚያገኙባቸው ቢሮዎች ፣ በትምህርት እና መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች እና በሌሎች የመብት ጥሰት ይደርስባቸዋል ተብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአምስቱ ላይ ባደረገው ክትትል፣ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ እንደሌላቸው ማረጋገጡን አስታወቀ
በኢትዮጵያ፣ በመንግሥት አካል ወይም በአካሉ እውቅና የሰዎችን ደብዛ የማጥፋት ድርጊት መጨመሩን ያስታወቀው ኢሰመኮ፣ በአፋጣኝ መቆም እንዳለበት አሳሰበ
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) «የተሰወሩ ሰዎች ሁሉ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ፣ በተሰወሩበት ጊዜ ሁሉ የተፈጸሙ ድርጊቶች ላይ የተሟላ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ» አሳስበዋል
ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው