የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን የማሻሻል ሂደት የባለድርሻ አካላትን ተቀራርቦ መሥራትና ቁርጠኝነት ይሻል
በክልሉ ማረሚያ ቤቶች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት ተጨማሪ ጥረት ያስፈልጋል
ኢሰመኮ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና በቀጣይ ተመሳሳይ ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ለማድረግ የሚያስችሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የሚያደርገውን ጥረት እና ውትወታ ይቀጥላል
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በግዳጅ የመከላከያ ሰራዊት አባል እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ብሏል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
ኮሚሽኑ ከኅዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ እና ሻሸመኔ ከተሞች እንዳካሄደ በገለጸው ክትትል እና ምርመራ፣ "የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ" በሚል ሕፃናትንና የአእምሮ ህሙማንን ጨምሮ የክልሉ ነዋሪዎች በግዳጅ መያዛቸውን አመልክቷል
ኢሰመኮ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ለመከላከያ ሰራዊት ምልመላ እናካሂዳለን በሚል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን በግዳጅ እንደያዙ እንዲሁም የተያዙትን ለመልቀቅ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስገደዳቸውን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ወደ ምርመራ ገብቻለሁ ብሏል
ኮሚሽኑ ምርመራውን በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማቆያ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በጉዳዩ ዙሪያ ቃለ መጠይቅ ማድረጉን ገልጿል
ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የክልሉ መንግሥት የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል
በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በግጭት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም በማድረግ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ በቁርጠኝነት እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በድጋሚ ጠይቋል