የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) «የተሰወሩ ሰዎች ሁሉ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ፣ በተሰወሩበት ጊዜ ሁሉ የተፈጸሙ ድርጊቶች ላይ የተሟላ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ» አሳስበዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመንግሥት የፀጥታ አካላት በማንኛውም ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ ሠልፎች እንዲሁም ሌሎች ስብስባዎች፣ ተመጣጣኝ ካልሆነና ሞት ከሚያስከትል የኃይል ዕርምጃ መውሰድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ
“መንግሥት የአስገድዶ መሰወር ወንጀል ሰለባ ለሆኑ ሰዎች መፍትሔ መስጠቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህንን ወንጀል ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተቀብላ እንድታጸድቅ ጥሪ እናቀርባለን” - የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ
ኢሰመኮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከደረሱት አቤቱታዎችና ጥቆማዎች በመነሳት ሲያደርግ በነበረው ክትትል መሠረት በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ጉዳይ እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል
የአስገድዶ መሰወር ወንጀልን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተቀብላ ልታጸድቅ ይገባል
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተከሰተው ድርቅ በየቦታው የሞቱ እንስሳት በአግባቡ እንዲወገዱ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ
በባሕርይ እና በማኅበራዊ ለውጥ ዙሪያ የሚሠሩ አካላት ብዝኃነትን ማዕከል በማድረግ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች በማስፋፋት ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እንዲሁም በሱማሌ ክልል ያለው የድርቅ ተፅዕኖ ተባብሶ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ