የፌዴራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በአፋጣኝ በመረጃና በምዝገባ ሥርዓት የታገዘ፣ አሳታፊ የሆነ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የተዘረጋለት እንዲሁም ከፍላጎት ጋር የተመጣጠነ ምላሽ ማቅረብ እና ክትትል ማድረግ፣ እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና ግልጋሎት እና በመጠለያ መብት ረገድ ያለውን ክፍተት በመለየት መብቶቹን ለማሟላት ተገቢውን እርምጃ በአፋጣኝ መውሰድ እና በመንግሥትና በአጋር ድርጅቶች ለድርቁ የሚሰጡ ምላሾች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ልዩ ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ ያስገቡ እንዲሆኑ ማድረግ ይኖርባቸዋል
የክልሉ መንግሥት ለሟች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ካሳ የከፈለ ቢሆንም ለተሟላ ፍትሕ የወንጀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል
Conflict flared up in Gedamaytu city on July 24
Appointments in line with recently amended EHRC establishment Proclamation No. 1224/2020, followed public nomination process through independent nomination committee which included the participation of civil society representatives
የሰብአዊ መብቶች ምርጫ ክትትል ቡድኖች በሚሰማሩባቸው ስፍራዎች በምርጫው እለት እና ከምርጫው በኋላ ባሉት ቀናት በምርጫ ጣቢያዎችም በመገኘት ምልከታ ያደርጋሉ
ኢሰመኮ በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት በገለልተኝነት ተግባራቸውን በመወጣት የዜጎች መብቶችን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ እንዲሁም ጥሰቶች ሲኖሩ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በአጽንዖት አሳስቧል
ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በመነደፍ ወይም በመካሄድ ላይ የሚገኙ ግጭት የተከሰተባቸውን አካባቢዎች መልሶ የማቋቋም ተግባራት በአካባቢዎቹ የሚኖሩና የሚያድጉ ሕጻናትን ያማከሉ እንዲሆኑ ጠየቀ
EHRC calls for nationwide policies and efforts of recovery and rehabilitation of post-conflict areas to be child-centred
የፌዴራልም ሆነ የክልል የቤተሰብ ሕግ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መርሆዎች እና ድንጋጌዎች ጋር የሚጣረስ ከሆነ እነዚህን የማኅበረሰብ ክፍሎች ለድርብ ተጋላጭነት ይዳርጋል
የፌዴራልም ሆነ የክልል የቤተሰብ ሕግ የሴቶችንና ሕጻናትን መብቶች ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጾ ቢኖረውም፣ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መርሆዎች እና ድንጋጌዎች ጋር የሚጣረስ ከሆነ እነዚህን የማኅበረሰብ ክፍሎች ለድርብ ተጋላጭነት ሊዳርግ ይችላል