ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች እና በጋሞ ዞን አስተዳደር መካከል ያለው አለመግባባት ውጥረት እየጨመረ መምጣቱን አመላክቷል
ከግጭቶቹ ጋር በተያያዘ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቂ የሆነ አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በአፋጣኝ ማቅረብን ጨምሮ፣ ተፈናቃዮች እና ነዋሪዎች ወደ ዘላቂ ሰላም የሚመለሱበት ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል
በአዲስ መልኩ በሚዋቀሩ አካባቢዎች የሚነሱ የደመወዝ እና ተያያዥ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት በጤና እና በትምህርት መብት እንዲሁም በአካባቢዎቹ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሉ ሥጋቶችን ይቀርፋል