በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓመታዊው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ዋነኛ ዓላማ (December 10) የሚውለውን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች ቀን ለማሰብ፣ የኪነ ጥበብን እና የሰብአዊ መብቶችን ትስስር ለማጠናከር፣ በሁለቱ ዘርፎች መካከል ያለውን ጥምረት በተመለከተ ግንዛቤ ለማስፋፋት፣ እንዲሁም ኪነ ጥበብ “ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን ማየት” የሚለውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ራዕይ ለማሳካት ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ለማስታወስ ነው።