በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ለማረጋገጥ እንደቻለው ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መተግበር ባለበት መንገድ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነፃ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ አለመተግበሩን ተመልክቷል።
ኢሰመኮ በማቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ወቅት ሰብአዊ መብቶችን የሚከታተል መሆኑንና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለኮሚሽኑ የክትትል ተግባራት ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ለማስታወስ ይወዳል