ተማሪዎቹ አገልግሎት በሚያገኙባቸው ቢሮዎች ፣ በትምህርት እና መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች እና በሌሎች የመብት ጥሰት ይደርስባቸዋል ተብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአምስቱ ላይ ባደረገው ክትትል፣ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ እንደሌላቸው ማረጋገጡን አስታወቀ
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም ከአመለካከት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ነጻ መሆን አለባቸው
በባሕርይ እና በማኅበራዊ ለውጥ ዙሪያ የሚሠሩ አካላት ብዝኃነትን ማዕከል በማድረግ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች በማስፋፋት ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው
የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ሂደት ሕጋዊ ሥርዓትን መከተልና በተለይ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት መከናወን አለበት
በቅርቡ ይፋ በተደረገው ‘‘የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አቅጣጫ አማራጮች’’ ሰነድ ዙሪያ በሚደረጉ ምክክሮችም ሆነ በሌሎች የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች የአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እና ተካታችነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል
ሰብአዊ ክብር፣ እኩልነት፣ አድሎ አለመፈጸም፣ ፍትሐዊነት እና አካታችነትን የመሳሰሉ መሠረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች እሴቶች፤ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ለአባሎቻቸው እና ለተጠቃሚዎች በሚሰጡት አገልግሎት ሊጠብቋቸው የሚገቡ እሴቶች ናቸው
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የከባቢያዊ፣ የአመለካከት፣ የተግባቦት እና ተያያዥ ተቋማዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል
መድሏዊ አሠራርን በማስወገድ አካታች የሥራ ቦታን መፍጠር የአካል ጉዳተኞችን የመሥራት መብት ለማክበርና ለማስከበር ያለው አስተዋጽዖ የጎላ ነው