አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ከተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶችና ከተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ወጥ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት ያስፈልጋል
ከግጭቶች በኋላ በሚከናወኑ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች የአካል ጉዳተኞችን እና የአረጋውያንን ትርጉም ያለው ተሳትፎ  ማረጋገጥ ያስፈልጋል
ከዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች ስምምነት ጋር የተጣጣመ ረቂቅ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች አዋጅ እንዲዘጋጅ፣ እንዲጸድቅ እና ወደ ሥራ እንዲገባ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ አለባቸው
ከዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች ስምምነት ጋር የተጣጣመ ረቂቅ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ ጸድቆ እንዲተገበር የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ርብርብ ይፈልጋል
የፍትሕ አካላትን የበጀት ውስንነት በመቅረፍ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት በቂ ትኩረት ይፈልጋል
የሚወጡ ሕጎች እና ፖሊሲዎች የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች ያማከሉ እና ልዩ ልዩ ፍላጎቶቻቸውን ያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
ውጤታማ እና ትርጉም ያለው የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎን ለማረጋገጥ የግምገማና የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት ቁልፍ ተግባራት ናቸው
ተማሪዎቹ አገልግሎት በሚያገኙባቸው ቢሮዎች ፣ በትምህርት እና መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች እና በሌሎች የመብት ጥሰት ይደርስባቸዋል ተብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአምስቱ ላይ ባደረገው ክትትል፣ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ እንደሌላቸው ማረጋገጡን አስታወቀ
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም ከአመለካከት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ነጻ መሆን አለባቸው