በባሕርይ እና በማኅበራዊ ለውጥ ዙሪያ የሚሠሩ አካላት ብዝኃነትን ማዕከል በማድረግ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች በማስፋፋት ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው
የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ሂደት ሕጋዊ ሥርዓትን መከተልና በተለይ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት መከናወን አለበት
የተሐድሶ አገልግሎት ለአካል ጉዳተኞች የሚደረግ እርዳታ ወይም ድጋፍ ሳይሆን ሰብአዊ መብት ነው
በቅርቡ ይፋ በተደረገው ‘‘የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አቅጣጫ አማራጮች’’ ሰነድ ዙሪያ በሚደረጉ ምክክሮችም ሆነ በሌሎች የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች የአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እና ተካታችነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል
የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት የአካል ጉዳተኞችን እና የአረጋውያንን ሰብአዊ መብቶች እንዲያስከብርና ፍላጎቶቻቸውን እንዲያሟላ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል
ሰብአዊ ክብር፣ እኩልነት፣ አድሎ አለመፈጸም፣ ፍትሐዊነት እና አካታችነትን የመሳሰሉ መሠረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች እሴቶች፤ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ለአባሎቻቸው እና ለተጠቃሚዎች በሚሰጡት አገልግሎት ሊጠብቋቸው የሚገቡ እሴቶች ናቸው
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የከባቢያዊ፣ የአመለካከት፣ የተግባቦት እና ተያያዥ ተቋማዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል
ፈራሚ ሀገራት (ዐይነ ስውራን) የሕይወትና የማኅበራዊ እድገት ክህሎት እንዲያገኙ፣ ብሎም በማኅበረሰባቸው ውስጥ ሙሉና ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል የብሬል ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ አለባቸው
State parties shall take appropriate measure to provide in buildings and other facilities open to the public signage in Braille and in easy to read and understand forms
መድሏዊ አሠራርን በማስወገድ አካታች የሥራ ቦታን መፍጠር የአካል ጉዳተኞችን የመሥራት መብት ለማክበርና ለማስከበር ያለው አስተዋጽዖ የጎላ ነው