የመንግሥት የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር አካላት በሙሉ በበቂ ምክንያት በወንጀል የተጠረጠረን ሰው በተለይም በቅድመ ምርመራ ወቅት የዋስትና መብት አጠባበቅ ሥርዓትን ባከበረ መንገድ ምርመራ ከማድረግ ውጪ ተገቢ ያልሆነ እስርን ማስወገድ አለባቸው
በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከተከሰተው ችግር ጋር በተያያዘ ግድያዎች፣ እስሮች፣ መዋከቦች እና እንግልቶች መፈጸማቸውን ኢሰመኮ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል
ኮሚሽኑ ከመደበኛው የክትትል እና የምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በሙሉ በማነጋገር እና በመመካከር ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና እንዲረጋገጡ የሚያስችል የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የመከላከል ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል