veryone has the right to education. Education shall be free, at least in the elementary and fundamental stages. Elementary education shall be compulsory
ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው፡፡ ቢያንስ የአንደኛ ደረጃና መሠረታዊ ትምህርት በነጻ ሊሰጥ ይገባል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ግዴታ ሊሆን ይገባል
ስልጠናዎቹ በሰብአዊ መብቶች እና የሽግግር ፍትሕ እንዲሁም በአካል ጉዳተኞች መብቶች፣ በሴቶች መብቶች፣ በሰብአዊ መብቶች ትምህርት ሥነ-ዘዴ፣ በተጠርጣሪዎች እና በሕግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው
ስልጠናዎቹ በሽግግር ፍትሕ እንዲሁም በአካል ጉዳተኞች፣ በሴቶች፣ በተጠርጣሪዎች እና በሕግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው
ለኹለት ዓመታት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ በርካታ ታዳጊዎችን ከትምህርት ገበታ ዉጪ እንዲሆኑ አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይ በአፍሪካ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚታሰበውን እና በየዓመቱ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 የሚውለውን የአፍሪካ ሳይንሳዊ ሕዳሴ ቀን (Africa Scientific Renaissance)፣ እንዲሁም የዓመቱ የትምህርት ወቅት መዝጊያን በማስመልከት በተዘጋጀ ማብራሪያ ትምህርት መሠረታዊ የሰብአዊ መብት መሆኑን በማስታወስ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በግጭት፣ በመፈናቀል፣ በአካል ጉዳት፣ በመሠረተ ልማት ውድመት፣ እንዲሁም በኑሮ ውድነት እና ሌሎች ምክንያቶች ከትምህርት ውጪ ሆነው ለበርካታ ወራት የቆዩ ሕፃናትን በ2016 ዓ.ም. ወደ ትምህርት እንዲመለሱ የማድረጉ ሥራ ከፍተኛ እና የተቀናጀ ትኩረት እንዲሰጠው ጥሪ ያቀርባል።
ስልጠናዎቹ ሰብአዊ መብቶችን እና የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን መሠረት በማድረግ የሰልጣኞችን ዕውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ለመገንባት ያለሙ ናቸው
በክልል ውድድሮች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ትምህርት ቤቶች ከግንቦት 12 እስከ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚካሄደው ሀገራዊ ውድድር ተሳታፊ ይሆናሉ
ተማሪዎችን ስለ ፍትሕ ሥርዓት ከማስተማሩም ባሻገር ለራሱና ለሌሎች ሰዎች መብቶች መከበር የሚቆም ትውልድን ለማፍራት ጉልህ ሚና አለው