Integrating the views and needs of victims is essential for an inclusive, responsive and effective transitional justice process
በቂ ምግብ የማግኘት መብት ምንድን ነው? በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዋና ዋና ይዘቶች (Components) ምንድን ናቸው? በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሕግ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ ስለ ምግብ መብት ምን ደንግጓል? ከበቂ ምግብ የማግኘት መብት የሚመነጩ ግዴታዎች ምንድን ናቸው?
ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እሥርን ጨምሮ ለመብት ጥሰት ምክንያቱ ግጭት በመሆኑ መፍትሔው ግጭቶችን በሰላም ማስቆም መሆኑን ሰሞኑን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል
ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር፣ በዐማራ ክልል ላይና እንዳስፈላጊነቱም በመላ ኢትዮጵያ ተፈጻሚ እንዲኾን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወጥቶ ለተጨማሪ ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ ዛሬ ረቡዕ የሚያበቃ ሲኾን፣ ከዐዋጁ ጋራ ተያይዞ በእስር ላይ የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠይቋል
በአማራ ክልል ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ የታሰሩ እንዲፈቱ፣ መደበኛ ሕግ ተግባራዊ እንዲሆን እና የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ
ምክንያቱን በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ያደረገው እና ለ10 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር በተያያዘ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ
ኮሚሽኑ ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 28፤ 2016 ባወጣው አጭር መግለጫ፤ “በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ” እና “ሌሎች ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች” ወደነበሩበት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል
በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎች ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል
በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክርቤት ያስተላለፈው የአስቸኳይ አዋጅ ተፈፃሚነት ማብቃቱን ተከትሎ በእስር ላይ የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል ሲል ኢሰመኮ አስታዉቋል