ስምምነቱ የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን ወደ ማኅበረሰቡ ከማስረጽ አኳያ ተደራሽነትን በመጨመር በኢትዮጵያ ዘላቂና ውጤታማ በሆነ መንገድ የሰብአዊ መብቶች ባህልን ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው
ኢሰመኮ በሕዝበ ውሳኔው ወቅት የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅን የሚከታተል የባለሙያዎች ቡድን ወደ ቦታው አሰማርቷል
ቅድመ ማስለቀቅ፣ በማስለቀቅ ወቅት እንዲሁም ድኅረ ማስለቀቅ ጊዜ መንግሥት ሊያሟላ የሚገባቸው የሰብአዊ መብቶች መርሆችን ያልተከተለ ሲሆን በኃይል ማፈናቀል እንደተፈጸመ ይቆጠራል፡፡ ይዞታ የማስለቀቅ ተግባር በአጠቃላይ ሰዎችን ቤት አልባ እንዲሆኑ እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ ማድረግ የለበትም
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የከባቢያዊ፣ የአመለካከት፣ የተግባቦት እና ተያያዥ ተቋማዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል
Everyone has the right to assemble and to demonstrate together with others peaceably and unarmed, and to petition
ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው
በስደተኞች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፤ በመንግሥት እና በተራድኦ ተቋማት ለስደተኞች የሚቀርቡ የሰብአዊ ድጋፍ እና ሌሎች አገልግሎቶች አካታች፣ ተደራሽ እና ሰብአዊ ክብራቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ይረዳል
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ ዙሪያ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ የተፈናቃዮችን ዘላቂ መፍትሔ የማመቻቸት ሥራዎች በበቂ የሕግ ማዕቀፍ እንዲደገፍ ከማስቻል ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው
ኢሰመኮ እንዳስታወቀዉ በየአካባቢዉ ስለሚፈናቀለዉ ሕዝብ በቂ መረጃ ባለመጠናቀሩ ለችግር ለተጋለጠዉ ተፈናቃይ የሰብዓዊ ድጋፎችን ለማቅረብ እንቅፋት ሆኗል
Education shall be provided in a manner that is free from any religious influence, political partisanship or cultural prejudices