The Commission’s resources mobilization efforts and partnerships come in support of its mandate
ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብት ሲባል ምን ማለት ነው? ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብት ጋር የተገናኙ ግዴታዎች ምንድን ናቸው?
ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት፣ ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀናት፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው
በቅርቡ ይፋ በተደረገው ‘‘የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አቅጣጫ አማራጮች’’ ሰነድ ዙሪያ በሚደረጉ ምክክሮችም ሆነ በሌሎች የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች የአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እና ተካታችነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ መሠረት "ከቤቶቹ ባለቤቶች ጋር በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ውይይት ተደርጎ በቂ ግንዛቤ" እንዲፈጠር መደረጉን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል
በዚህ ወር ውስጥ ብቻ በጥቂቱ ዘጠኝ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲሁም የሚዲያ ዐዋጁን በሚጻረር መልኩ መታሰራቸውን የኢትዮጵያ ሰባአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል
የሕግ ተጠያቂነት ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ተጎጂዎች በቂ ካሳና ማካካሻ እንዲያገኙ እና የመብቶች ጥሰቱ እንዳይደገም ማድረግ ተገቢ ነው
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ማህበር በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ መንግስት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እስር እና እንግልት እንዲያቆም ጠይቋል
የመንግስት የጸጥታ አካላት በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላት እንዲሁም በማህበረሰብ አንቂዎች ላይ ካተኮረ “እስር እና ማዋከብ” እንዲቆጠቡም ኮሚሽኑ ጠይቋል
ኢሰመኮ ከመደበኛው የክትትል እና ምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ምክረ ሐሳቦችን በመስጠት የተፈጠረው ችግር በውይይት እንዲፈታ ጥረት እያደረገ ይገኛል