ይህ የሩብ ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተለይ በግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ በሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና አሳሳቢነታቸው በቀጠሉ ጉዳዮች ላይ አጠቃላይ ምልከታ በመስጠት ለሰብአዊ መብቶች ሁኔታ መሻሻል ምክረ-ሐሳቦችን የሚያቀርብ ነው
ምክረ ሐሳቦች እንዲፈጸሙ ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሠሩ፤ በክልሉ መንግሥት እየተወሰዱ ያሉ አበረታች እርምጃዎችም ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል ለሚባሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች ነጻ የሕግ ድጋፍ፣ የመጠለያ፣ የጤና፣ የማኅበራዊና የሥነልቦናዊ አገልግሎት በመስጠት የሰብአዊ አገልግሎቱን የተሟላ ለማድረግ ያስችላል
በክልሉ ከሚስተዋሉ ፈታኝ ሁኔታዎች አንፃር የሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች አበረታች ቢሆኑም ሴት ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች የሚያዙበት ቦታ አለመለየትና ቅድሚያ አለመስጠት ለተጨማሪ የመብቶች ጥሰት ያጋልጣቸዋል