የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ባለፈው ሳምንት በነበረው ተቃውሞ፣ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እንዳረጋገጠ ገልጾ፣ የጸጥታ ኃይሎች ያልተመጣጠነ የኃይል ርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠቡ ጠይቋል
የመንግሥት የጸጥታ አካላት አላስፈላጊና ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል የመጠቀም አዝማሚያ እየጨመረ መምጣቱን እና በዚህም ሳቢያ በሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል እና የሥነ ልቦና ጉዳት እንዲሁም ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየደረሱ ናቸው
ባለፈው ሳምንት በአንዋር መስጂድ የሞቱና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በተመለከተ መንግስት ጉዳቱን የሚያጣራ ቡድን ማቋቋሙንም አረጋግጫለሁ ብሏል በመግለጫው