የሰንዳይ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ማዕቀፍ (እ.ኤ.አ. 2015-2030) በ187 አባል ሀገራት በ3ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ጉበኤ እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን በ2015 ጸድቋል። ይህ ማዕቀፍ መንግሥታት በቀዳሚነት የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ላይ ማተኮር እንዳለባቸው በመግለጽ፣ ኃላፊነቱ በዋነኛነት መንግሥት ላይ የሚወድቅ ቢሆንም ሁሉም ማኅበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ሥራዎች ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው ያስረዳል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ የደረሰው የመሬት ናዳ አደጋን ተከትሎ በሰዎች ሕይወት ላይ፣ በመኖሪያዎቻቸው እና በመተዳደሪያዎቻቸው ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የሚደርሱት ጥቆማዎች እና ሪፖርቶች በእጅጉ አሳሳቢ ናቸው ብሏል