የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል ለሚባሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች ነጻ የሕግ ድጋፍ፣ የመጠለያ፣ የጤና፣ የማኅበራዊና የሥነልቦናዊ አገልግሎት በመስጠት የሰብአዊ አገልግሎቱን የተሟላ ለማድረግ ያስችላል
በክልሉ ከሚስተዋሉ ፈታኝ ሁኔታዎች አንፃር የሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች አበረታች ቢሆኑም ሴት ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች የሚያዙበት ቦታ አለመለየትና ቅድሚያ አለመስጠት ለተጨማሪ የመብቶች ጥሰት ያጋልጣቸዋል
የፖሊስ አባላት በሥራቸው አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችን ለመለየት እና ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ስትራቴጂ የመንደፍ ክህሎት በተግባር እንዲለማመዱ ስልጠናው ምቹ እድል ፈጥሯል