በሁሉም ደረጃዎችና በሁሉም የትምህርት ዘርፎች በተለይም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለሴቶች የሚሰጡ ትምህርትና ስልጠናዎችን ለማስፋፋት ዝርዝር አወንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው
የሴቶች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ለማሻሻል የማኅበራዊ ሚዲያና የኪነጥበብ ይዘት ፈጣሪዎችን ማሳተፍ የጎላ አስተዋጽዖ አለው
በሃዲያ ዞን ግርዛትን ለማስቀረት ተጀምረው የነበሩ የመከላከልና የንቅናቄ ሥራዎች መቀነስ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ግርዛት ስርጭት እንዲጨምር አስተዋጾ አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል
በጋምቤላ ክልል የቤተሰብ ሕግ አፈጻጸም የታዩ ክፍተቶችን በሚገባ ለመመለስ ሕጉ የማኅበረሰቡን ወግ፣ ባህል፣ እሴቶች እና የአኗኗር ዘይቤ እንዲሁም ኅብረተሰቡ አሁን ያለበትን የእድገት ደረጃ ያማከለ ሆኖ መሻሻል ያስፈልገዋል
አብዛኛዎቹ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር የሚከወኑ ስራዎች ከድንበር ማሻገር ያሉት ላይ ያተኮረ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል
በሀገር ውስጥ በሴቶች እና በሕፃናት የመነገድ ድርጊትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሁሉን አቀፍ ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ማኅበራዊ ስልቶች ሊነደፉ ይገባል
Every woman shall be entitled to respect for her life and the integrity and security of her person. All forms of exploitation, cruel, inhuman or degrading punishment and treatment shall be prohibited
ማንኛዋም ሴት ለሕይወቷ እና ለአካል ደኅንነቷ ክብር የማግኘት መብት አላት፡፡ ሁሉም ዐይነት ብዝበዛ፣ ጨካኝ፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም ክብርን የሚያዋርድ ቅጣት እና አያያዝ የተከለከለ ነው
The collective efforts of international, continental, and national institutions are essential to safeguard and promote children's rights across the African continent
ሁሉም ሕፃናት በሕይወት የመኖር፣ ወላጆቻችውን ወይም በሕግ የማሳደግ መብት ያላቸውን ሰዎች የማወቅና የእርነሱንም እንክብካቤ የማግኘት መብቶች አሏቸው