Every young person shall have the right to social, economic, political and cultural development with due regard to their freedom and identity and in equal enjoyment of the common heritage of mankind
ማንኛውም ወጣት ነጻነቱንና ማንነቱን እንዲሁም በሰው ልጅ የጋራ ቅርስ እኩል ተጠቃሚነቱን ባከበረ መልኩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ባሕላዊ እድገት የማግኘት መብት አለው
ማንኛውም ወጣት በሁሉም የማኅበረሰብ ዘርፎች ውስጥ የመሳተፍ መብት አለው
Every young person shall have the right to participate in all spheres of society
አባል ሀገራት ለወጣቶች ሁለንተናዊ እድገትን የሚያረጋግጥ በቂ የሆነ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት ዕውቅና ሊሰጡ ይገባል
State parties shall recognise the right of young people to a standard of living adequate for their holistic development
ስልጠናው ወጣቶች በሰላም በጋራ መኖርን እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ካሉ ልዩነቶችን መሰረት አድርገው የሚከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመከላከል ሥራ ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማስቻል አላማ ያለው ነው፡፡