"በሲቨል ሰዎች ላይ ግድያ በፈጸሙና በዘፈቀደ እስራት ላይ በተሳተፉ አካላት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ" - የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎችና የዘፈቀደ እስሮች “እጅግ አሳሳቢ” ኾነዋል ሲል ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል
በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች “የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል አምጡ” በሚል በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
Ethiopia's human rights body has accused federal government forces of carrying out extra-judicial killings in the restive region of Amhara and mass arbitrary detentions
የቁም ነገር መጥሄት ባልደረቦች ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የሄደባቸውን መንገዶች እንዲሁም ያወጣቸውን ተከታታይነት ያላቸውን ሪፖርቶች መርምረው ዶ/ር ዳንኤልንና የሚመሩትን ኮሚሽን በዓመቱ ሃላፊነቱን በአግባቡ የተወጣ የመንግስት መስሪያ ቤት ብለዋቸዋል
የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እንደተናገሩት፣ በግጭቶች እና ጥቃቶች ሳቢያ በዜጎች በሕይወት የመኖር እና የመንቀሳቀስ መብት ላይ እየደረሰ ያለው ጥሰት አሳሳቢ ነው
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ም/ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት አባል ዶ/ር ካሣ ተሻገርን ጨምሮ 53 ሰዎች አዋሽ አርባ ውስጥ ባለ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ መታሰራቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋገጠ
ኮሚሽኑ ይህን ያለው ዋና ኮሚሽነሩ ዳንዔል በቀለን ጨምሮ አምስት የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. መጎብኘቱን አስመልክቶ ዛሬ ነሐሴ 27 ባወጣውና ለአሻም በላከላት መግለጫ ላይ ነው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዋሽ አርባ በሚገኘው የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በእሥር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን መጎብኘቱን ትናንት ቅዳሜ ነሐሴ 27 ባወጣው መግለጫ አስታወቀ
አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን እነዚህን ታሳሪዎች፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 5 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ትላንት ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. መጎብኘታቸው በመግለጫው ተጠቅሷል