Criminal liability of persons who commit crimes against humanity, so defined by international agreements ratified by Ethiopia and by other laws of Ethiopia, such as genocide, summary executions, forcible disappearances or torture shall not be barred by statute of limitation
ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር፣ ወይም ኢ-ሰብአዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም
በተለይም ሴት ሕፃናት የመማር መብታቸውን ከማጣታቸው አልፎ ለ ያለ ዕድሜ ጋብቻ እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸው፣ ወደ ከተማ እየፈለሱና ለጉልበት ብዝበዛ እየተዳረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ አመልክቷል
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ባሉ ግጭቶች እና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ከ5500 በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራቸውን ከማከናወን ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
ኢሰመኮ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች መካከል በፖሊስ ጣቢያዎች እና በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎችን የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን በተመለከተ የመከታተልና ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ ከተቋሙ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል
በ2016 ዓ.ም. በበርካታ የኢትዮጵያ አከባቢዎች በተለምዶ ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ምክንያቶች ሳቢያ ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉበት በርካታ ክስተቶች መመዝገቡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
ኮሚሽኑ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው 3ኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ይፋ አድርጓል
ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት በሀገራዊ ቋንቋዎች መተርጎም የስምምነቱን ተደራሽነት በማስፋት ለአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች መከበር አስተዋጽዖ አለው
Trafficking in human beings for whatever purpose is prohibited
ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው