የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያራዝመው ከሆነ በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ሊያስከትል የሚችለው አሉታዊ ተጽእኖ አሳሳቢ ነው ብለዋል
የመንግሥት አስተዳደር ሥልጣን መሠረቱ የሕዝብ ፍቃድ መሆን ይኖርበታል፤ የሕዝቡ ፍቃድ የሚገለጸውም በተወሰኑ ጊዜያት በሚካሄዱ ሐቀኛ ምርጫዎች ነው
The will of the people shall be the basis of the authority of government; this will shall be expressed in periodic and genuine elections
በበጀት አመዳደብ ሂደት ሰብአዊ መብቶች ተኮር መሆን ማለት ሀብትን የሰው ልጆችን ባስቀደመ መልኩ ወይም ሰዎችን ማዕከል በሚያደርግ መንገድ መመደብ ነው
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነጻነት አለው
Any Ethiopian or foreign national lawfully in Ethiopia has, within the national territory, the right to liberty of movement and freedom to choose his residence, as well as the freedom to leave the country at any time he wishes to
የጤና መብት እና በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት በተሻለ ሁኔታ እንዲተገበሩ ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሠሩና የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል
በምግብ ሥርዓቱ ውስጥ ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን እና ሊጣሱ የሚችሉ መብቶችን መለየት ሰብአዊ መብትን መሠረት ያደረገ የምግብ አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል
በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ኤልጎ፣ ወዘቃ፣ ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ ጊዜ ጥያቄ ሲያነሱ የቆዩ ሲሆን፤ በተለይ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ውዝግቡ እየተባባሰ እንደመጣ ተገልጿል
ከኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጋር የተደረገ ቆይታ