ማንኛውም ሰው በቀረበበት የወንጀል ክስ በተገኘበት የመዳኘት እና ራሱን በግሉ ወይም በመረጠው ጠበቃ በኩል የመከላከል፣ ጠበቃ ከሌለው ይህ መብት ያለው መሆኑ እንዲገለጽለት መብት አለው
ሴቶች ሠራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው
Women workers have the right to equal pay for equal work
States shall have the duty, individually or collectively, to ensure the exercise of the right to development
ሀገራት በተናጠልም ሆነ በጋራ የልማት መብትን ተግባራዊነት የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው
የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ እና ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች በቂ ትኩረት በሚሰጥ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ሊያደርጉ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማእከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በተለይም ከአዳዲስ የክልል አደረጃጀቶችና መዋቅሮች መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ የደመወዝ መዘግየትን እና ያለመከፈልን የተመለከቱ አቤቱታዎችን እና ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ምርመራ በማከናወን ታኅሣሥ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ሪፖርት (ከዚህ በኋላ “ዋናው የምርመራ ሪፖርት”) ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚሁ መሠረት፣ ከ2012 ዓ.ም....
ሃይማኖትንና እምነትን የመግለጽ መብት ሊገደብ የሚችለው የሕዝብን ደኅንነት፣ ሰላምን፣ ጤናን፣ ትምህርትን፣ የሕዝብን ሞራል፣ የሌሎች ሰዎችን መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ለማስጠበቅ እና መንግሥት ከሃይማኖት ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ሕጎች ይሆናል
Freedom to express or manifest one's religion or belief may be subject only to such limitations as are prescribed by law and are necessary to protect public safety, peace, health, education, public morality or the fundamental rights and freedoms of others, and to ensure the independence of the state from religion
በዚህ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሲቪልና የፖለቲካ እንዲሁም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት፥ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉን ተከትሎ ለግል ድርጅት ተቀጣሪ ሰራተኞችም የደሞዝ ማሻሻያ መደረጉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል