ከምርጫው ጋር የተገናኙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጥቆማዎችና አቤቱታዎች ለሰብአዊ መብቶች ክትትል ባለሙያዎች፣ በአቀራቢያ በሚገኙ የኢሰመኮ የከተማ ጽሕፈት ቤቶች በአካል በመገኘት ወይም በነጻ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወል ማቅረብ ይቻላል
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሠረተ ልዩነት ሳይደረግበት በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት አለው
Every Ethiopian national, without any discrimination based on colour, race, nation, nationality, sex, language, religion, political or other opinion or other status, has the right to vote and to be elected at periodic elections to any office at any level of government
ዚህ ሪፖርት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ የበጀት ዓመት አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም. ያከናወናቸው ዐበይት ተግባራት እና የተገኙ ውጤቶች ቀርበዋል። በተጨማሪም የኮሚሽኑን የፋይናንስ አጠቃቀም መግለጫ እና በዕቅድ አፈጻጸም ያጋጠሙ ችግሮች ትካትተዋል። ተግባራቱ ኮሚሽኑ በአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱ ለይቶ ባስቀመጣቸው ዘጠኝ የትኩረት መስኮች መሠረት የተደራጁ ናቸው፡፡  
This report presents the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC/the Commission)’s major activities and results for the Ethiopian fiscal year 2022/23. It also includes a financial report for the period, as well as the challenges the Commission faced. The activities are organized into nine program areas, which align with the Commission’s focus areas as identified in...
የቁም ነገር መጥሄት ባልደረቦች ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የሄደባቸውን መንገዶች እንዲሁም ያወጣቸውን ተከታታይነት ያላቸውን ሪፖርቶች መርምረው ዶ/ር ዳንኤልንና የሚመሩትን ኮሚሽን በዓመቱ ሃላፊነቱን በአግባቡ የተወጣ የመንግስት መስሪያ ቤት ብለዋቸዋል
ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው ቦታዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች ውጭ አጠቃላይ ሕዝበ ውሳኔው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎላ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ነጻ የነበረ ነው
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሥር መንስኤ የሆኑ የተጠያቂነት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት መላላት እና የሰላም እና ደኅንነት እጦት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት የመንግሥት ከፍተኛ እና ያልተቋረጠ ጥረት ያሻል (የ2015 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት)
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት ኮሚሽኑ ባደራጃቸው ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና የከተማ ጽሕፈት ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በጥቅሉ የሚዳስስ ነው፡፡ ሪፖርቱ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በለያቸውና በሚሠራባቸው የትኩረት ዘርፎች (Thematic Areas) ላይ መሠረት ያደረገ ሲሆን በሪፖርቱ...
ይህ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፓርት ከሰኔ 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን፣ በልዩ ልዩ የኢሰመኮ የሥራ ዘርፎች እና ጽ/ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ባለፉት አሥራ አንድ  ወራት የነበረውን ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የሚዳስስ ነው፡፡ ሪፖርቱ ኢሰመኮ በሚንቀሳቀስባቸው የሥራ ዘርፎች የተስተዋሉቁልፍ እመርታዎችን እና  ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ እንዲሁም አንኳር ምክረ-ሐሳቦችን...