ወቅታዊ እና ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳዎችን ተገንዝቦ አስተዋፆ የማድረግ ዐቅም ያለው ትውልድ በማፍራት ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይቻላል
A child temporarily or permanently deprived of his or her family environment, or in whose own best interests cannot be allowed to remain in that environment, shall be entitled to special protection and assistance provided by the State
ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከቤተሰቡ የተለየ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲባል ከቤተሰቡ ጋር እንዲቆይ ሊደረግ የማይችል ሕፃን የመንግሥትን ልዩ ጥበቃ እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው
ዋና ኮሚሽነሩ ይህንን ኃላፊነት ከያዙ አምስት ዓመታት ሞልተው የመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ሊጠናቀቅ ወራት ቀርተዋል፡፡ ሲሳይ ሳህሉ ከዋና ኮሚሽነር ዳንኤል ጋር በተቋሙና በአጠቃላይ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና ምልከታ ላይ ያደረገው ቃለ ምልልስ
Any media financed by or under the control of the State shall be operated in a manner ensuring its capacity to entertain diversity in the expression of opinion
በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል
ውድድሩ በሽግግር ፍትሕ ሂደት ታሳቢ ሊደረጉ በሚገቡ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን 81 ትምህርት ቤቶች ተሳታፊ ሆነዋል
የወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ማዳበር በሽግግር ፍትሕ ሂደት አወንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ያግዛል
ሁሉም የሰው ልጆች እኩል ክብርና መብቶች ይዘው ነጻ ሆነው ተፈጥረዋል
All human beings are born free and equal in dignity and rights