ያቀረባቸው ምክረ ሃሳቦች እንዲፈጸሙ የጣምራ ምርምር ቡድኑ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል
በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ኅዳር በከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት ላይ በተፈፀመው ጥቃትና ግድያ ውስጥ "የፀጥታ ኃይሎች እጅ አለበት" የሚያስብል በቂ መሠረት አለ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ታስረው እስካሁን ያልተለቀቁት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ
ለሟቾች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ለደረሰባቸው ጉዳት ተገቢ የሆነ ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል
ጥር 14 ፣ 2014 ዓ.ም.፣ ጅግጅጋ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር የሕግ ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አድንቋል።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግስት የቀረበለትን ውሳኔ ሃሳብ በአፋጣኝ እንደሚያጸድቀው ኮሚሽኑ ተስፋውን እየገለጸ፤ የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ አሁንም በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጥሪውን ያቀርባል
ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የጤና ችግር ያለባቸው እና ሌሎች ጉዳያቸው ተጣርቶ በቀላል ዋስትና የተለቀቁ ሰዎች ይገኙበታል
ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።
በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ለማረጋገጥ እንደቻለው ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መተግበር ባለበት መንገድ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነፃ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ አለመተግበሩን ተመልክቷል።