ሪፖርቱ በአገር ውስጥም በዓለም አቀፍ ደረጃም ጥሩ ምላሽና ተቀባይነት አግኝቷል ብዬ አምናለሁ።
የተፈጸሙ ጥሰቶች የጦር ወንጀል ስለመሆናቸው አመላካች ሁኔታዎች አሉ
በጦርነቱ ወቅት ትግራይ ውስጥ “ተፈጽመዋል” የተባሉት የሰብዓዊ መብት ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን፣ የስብዕና እና የስደተኛ ሕግጋት መጣስ ሲያጣራ የቆየው ጥምር መርማሪ ቡድን ባወጣው የግኝቱ ሪፖርት የጦር ወንጀሎች እና በስብዕና ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎች በሁሉም ወገኖች ስለመፈጸማቸው አሳማኝ መሰረቶች አሉ ብሏል።
ኢሰመኮ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ባደረገው ውይይት የታሳሪዎችን ደህንነት ስለማረጋገጥ መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ላይ ተመካክሯል
ጊዳ ኪራሙ ወረዳን ጨምሮ በተለያዩ የምስራቅ ወለጋ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በአስጊ ሁኔታ ይገኛሉ
በተለይም በአሁኑ ወቅት ከሴዳል ወረዳ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሸሽተው የሚገኙ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት፣ ከጥር ወር 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በወረዳው በሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ነዋሪዎች የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ከመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዝግ ሆነው ቆይተዋል።
አጥፊዎቹ ሕግ ፊት መቅረብ አለባቸው