ኮሚሽኑ ምርመራውን በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማቆያ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በጉዳዩ ዙሪያ ቃለ መጠይቅ ማድረጉን ገልጿል
ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የክልሉ መንግሥት የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ የሪጅን ዳሬክተር የሆኑት ሰላማዊት ግርማይ ኢሰመኮ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ስለሚያከናውናቸው ተግባራት፤ እንዲሁም በዋነኝነት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ ክትትልና ምርመራ በማድረግ ለጥሰቶቹ መፍትሔ ለማፈላለግ የሚያከናውናቸውን ተግባራትና ስለሚሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አስረድተዋል
The latest report from the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) calls on officials to avert what it called a disturbing rise in forced disappearances, primarily in the Amhara and Oromia regions
ጉዳዩን በሚመለከት ጥብቅ ክትትል አድርጌያለሁ ያለው ኮሚሽኑ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የቆዩ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ከ50 በላይ ሰዎችን የተመለከቱ አቤቱታዎችን መመርመሩን አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ሳይታወቅ፣ መደበኛ ባልሆነ ቦታ እንዲቆዩ ተደርገዋል ያሉ ሰዎችን በተመለከተ ዛሬ ሪፖርት ያወጣው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፣ 52 ሰዎችን የተመለከቱ አቤቱታዎችን መመርመሩን አስታውቋል
ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ “በተራዘመ እስር”፣ “መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ቦታዎች”፣ እንዲሁም “በአስገድዶ መሰወር ሁኔታ“ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ሁኔታ፤ “አሳሳቢ” ሆኖ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የቆዩ ከ52 በላይ ሰዎችን የተመለከቱ አቤቱታዎች መቀበሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ለአራዳ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል
መደበኛ ባልሆነ ማቆያ ቦታ፣ ያሉበት ሳይገለጽ እንዲቆዩ የተደረጉ እና አስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎች እና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በተመለከተ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እና ፍትሕ ሊሰጣቸው ይገባል ሲል ኢሰመኮ ገለጸ
ኢሰመኮ ከ2015 ዓ.ም. ሐምሌ ወር ጀምሮ “በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የቆዩ” ከ52 በላይ ሰዎችን የተመለከቱ አቤታዎችን መመርመሩን ገልጿል