በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እና መፈናቀል እልባት ለመስጠት የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት በዞኑ በቂ የጸጥታ አካላትን ማሰማራትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ጨምሮ አፋጣኝ፣ ተጨባጭና ዘላቂ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል
The Federal Government and the Oromia Regional Government shall take immediate, concrete, and lasting measures, including the deployment of adequate security forces and ensuring accountability, to address killings, bodily injuries, destruction of property and displacement in various areas of Arsi Zone, Oromia Region
በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ችግሩን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እና ልዩነቶችን በሕግ መሠረት በምክክርና በመግባባት ለመፍታት እንዲሠሩ ኢሰመኮ ያሳስባል
EHRC urges all parties involved in the conflict to refrain from actions that exacerbate the situation and to resolve differences through consultation and mutual understanding, in accordance with the law
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ፣ ጎንደር እና ኮምቦልቻ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን አስመልክቶ በ2017 ዓ.ም የሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ታኅሣሥ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ወይይት ማድረጉን ተናግሯል
በክልሉ ያለውን የታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን ለማሻሻል በትኩረትና በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል
በማእከሉ ያለውን መጨናነቅ ለመቀነስ፣ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላትና አገልግሎቶችን ለማሻሻል ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች በተመለከተ ምክረ ሐሳብ ቀርቧል
መልካም እመርታዎችን በማስቀጠቅል እና ጉድለቶችን በመሙላት አበረታች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን ለማጠናከር ተቀራርቦ መሥራት ያስፈልጋል
ክልሉ የነዋሪዎቹን ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው