ጥቃቱ የተፈጸመው በግልገል በለስ ከተማ፣ በተለምዶ “ቻይና ካምፕ” ተብሎ በሚጠራ ሰፈር ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን፣ 3 የአካባቢውን ሚሊሻ አባላት ጨምሮ 8 ነዋሪዎች መገደላቸውን፣ በ16 ሲቪል ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን፣ በርካታ ሌሎች ነዋሪዎች ቻይና ካምፕን ለቀው ወደ ሌላ ሰፈር መሸሻቸው ታውቋል
በመተከል ዞን ከሰሞኑ የተፈጠረው ጥቃትም የዚህ ማሳያ ነው ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መንግስት የሰላም ሂደት አፈፃፀሙን እንዲከውን አሳስቧል
በማረሚያ ቤቶች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቂ በጀት፣ ወጥ የታራሚዎች አያያዝና አጠባበቅ ሕግ ያስፈልጋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት ምርመራ እያደረግን ነው፤ ለጊዜው ግን ንጹሃን ዜጎች እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በታጣቂው መገደላቸውን አረጋግጠናል ብለዋል
በኢትዮጵያ የዜጎች አስገድዶ መሰወር፣ ተጠርጣሪዎችን በጭካኔ፣ በአዋራጅ እና ኢሰብዓዊ በሆነ መልኩ አያያዝ መጨመሩን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
በኢትዮጵያ፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እጅግ አሳሳቢ ኾኖ መቀጠሉን የገለጸው ኢሰመኮ፣ ለመባባሱ ዋና ምክንያት ነው ያለው ትጥቃዊ ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጠየቀ
የመተከል ዞን ሰላም እና ደኅንነት ዘላቂ በሆነ መልኩ እንዲመለስ የተጀመሩ የሰላም ሂደቶችን አፈጻጸምና ውጤት መከታተል ይገባል
የታጠቁ ሰዎች እንቅስቃሴዎችና ግጭቶች አሁንም ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት እየሆኑ ነው
ሰዎች በሰላም ወጥቶ የመግባት፣ ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ እና የመሥራት መብቶቻቸው እንዲከበሩና መልካም እመርታዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው የትጥቅ ግጭቶችን ግልጽ እና አካታች በሆነ ሂደት ማስቆም፣ በቁርጠኝነት የሕግ የበላይነትን ማስከበር ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽኑ/ኢሰመኮ/ ከሰኔ 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ያለውን የሃገሪቱን የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ የተመለከተ ሪፖርት ይፋ አድርጓል