የሰው ሕይወት በተቀጠፈበት የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ የፀጥታ ኃይሎች አላስፈላጊ እና ከመጠን ያለፈ እርምጃ መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
ከልክ ያለፈ ድርጊት ፈጽመዋል ያላቸው የጸጥታ ኃይሎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የጠየቀው ኢሰመኮ በክብረ በዓላት አከባበር ላይ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ የሕግ አስከባሪዎች አስፈላጊ ሥልጠና እንዲያገኙ ሊደረግ ይገባልም ብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ፣ በበዓሉ ላይ የተከሰቱትን ክስተቶች አስመልክተው በሰጡት ሀሳብ፣ የጸጥታ ኃይሎች በዓሉን ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ከልክ ያለፈ አላስፈላጊ ድብደባ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ ጥይትና ሌሎች ከመጠን ያለፉ እምጃዎችን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል
የኢሰመኮ የሕግና ፖሊሲ ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ታሪኳ ጌታቸው ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት፣ “የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ከልክ ያለፈ እርምጃ ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን አረጋግጠናል” ብለዋል
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በበዓሉ ላይ የተከሰቱትን ክስተቶች አስመልክተው በሰጡት ሀሳብ፣ የጸጥታ ኃይሎች በዓሉን ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ከልክ ያለፈ አላስፈላጊ ድብደባ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ ጥይትና ሌሎች ከመጠን ያለፉ እምጃዎችን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል
Implicated law enforcement officials must be subject to accountability and law enforcement officers should be adequately trained to avoid similar incidents
በአፋር ክልል በጦርነት ምክንያት ለተደጋጋሚ መፈናቀል የተጋለጡ የሁለት ዞን ነዋሪዎች ለከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ መጋለጣቸው ተገለጠ። በተጨማሪም የንግድ እንቅስቃሴው ገደብ በመኖሩ ላልተገባ ኢኮኖሚያዊ ጫና መጋለጣቸውን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ አለመደረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባደረገው ክትትል ማረጋገጡን አስታወቀ
ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ እውነትን ለማውጣት፣ ማኅበረሰባዊ እርቅ እና ፈውስ ለማምጣት እንዲሁም የተጎጂዎችን መፍትሔ የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ተግባራዊ መደረግ አለበት
መንግሥት በአፋር ክልል በዞን ሁለት፣ በዞን አራት እንዲሁም በሰመራ ከተማ ለሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ተመላሾች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ የሆነ የሰብአዊ ድጋፍ የማቅረብ ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ መወጣት አለበት
ስምምነቱ “የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የሲቪክ ማኅበራትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በሕዝባዊ ምክክር የሚገኙ ግብአቶችን መሠረት አድርጎ እና መደበኛ ሀገራዊ የፖሊሲ አወጣጥ ሂደቶችን ተከትሎ ሊዘጋጅ እንደሚገባ” ያስቀምጣል