በኦሞ ወንዝ የላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች ከነሐሴ ወር የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ በሆነው የኦሞራቴ ከተማ እንዲሁም ቻይና ካምፕ በተባሉ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ በውሃ የመጥለቅለቅ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል ብሏል
የታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲከበሩ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በተጨማሪ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ አስተዋጽዖ ሊያደርጉ ይገባል
የታራሚዎችንና የተጠርጣሪዎችን ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ለማሻሻል ምክረ ሐሳቦችንና የተደረሱ ስምምነቶችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መተግበር ያስፈልጋል
የክልሉን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል በጎ ጅምሮችን ማጠናከር እንዲሁም በክትትል እና ምርመራ ግኝቶች መሠረት የቀረቡ ምክረ ሐሳቦችን መተግበር ያስፈልጋል
በ2016 ዓ.ም. በበርካታ የኢትዮጵያ አከባቢዎች በተለምዶ ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ምክንያቶች ሳቢያ ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉበት በርካታ ክስተቶች መመዝገቡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
የሰብአዊ መብቶች ምርመራ እና የወንጀል ምርመራ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው? የሁለቱ የምርመራ ዐይነቶች ዓላማዎችና ግቦች ምንድን ናቸው? በሁለቱ የምርመራ ዘርፎች መካከል ያለው የማስረጃ ምዘና ስልት ልዩነት ምን ይመስላል? ሁለቱ የምርመራ ዘርፎች የሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ ለማሻሻል በምን መንገድ ሊደጋገፉ ይችላሉ?
የሰብአዊ መብቶች ምርመራ እና የወንጀል ምርመራ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው? የሁለቱ የምርመራ ዐይነቶች ዓላማዎችና ግቦች ምንድን ናቸው? በሁለቱ የምርመራ ዘርፎች መካከል ያለው የማስረጃ ምዘና ስልት ልዩነት ምን ይመስላል? ሁለቱ የምርመራ ዘርፎች የሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ ለማሻሻል በምን መንገድ ሊደጋገፉ ይችላሉ?    
በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክልሎች በታጣቂ ኃይሎች እና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተወሰዱ ርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርስ የሞት እና የአካል ጉዳት አሳሳቢ መሆኑ ተገለጠ ። ይህንን እና ሌሎች ብርቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) በዓመታዊ ዘገባው ይፋ አድርጓል
በማቆያዎች እና በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለውን መጨናነቅ እና አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል አማራጭ ቅጣቶችን ጨምሮ ሌሎች የፖሊሲ አማራጮችን መተግበር ይጠይቃል
በጾታ የተለየ ማደሪያ ክፍል እና ለሴቶች ቅድሚያ የሚሰጥ አሠራር አለመኖር ሴት ተጠርጣሪዎችን እና ታራሚዎችን ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያጋልጣል