ይህ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፓርት ከሰኔ 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን፣ በልዩ ልዩ የኢሰመኮ የሥራ ዘርፎች እና ጽ/ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ባለፉት አሥራ አንድ ወራት የነበረውን ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የሚዳስስ ነው፡፡ ሪፖርቱ ኢሰመኮ በሚንቀሳቀስባቸው የሥራ ዘርፎች የተስተዋሉቁልፍ እመርታዎችን እና ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ እንዲሁም አንኳር ምክረ-ሐሳቦችን...
የፍትሕ አካላትን የበጀት ውስንነት በመቅረፍ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት በቂ ትኩረት ይፈልጋል
የሚወጡ ሕጎች እና ፖሊሲዎች የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች ያማከሉ እና ልዩ ልዩ ፍላጎቶቻቸውን ያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ከፍትሕ ተቋማት ሥራዎች ባሻገር ማኅበረሰቡ በጉዳዩ ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ ትልቅ ሚና አለው
በኢትዮጵያም አረጋውያን ለመሰል የመብት ጥሰት ይጋለጣሉ የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተቋማት በአረጋውያን ዙሪያ እንዴት እየሰሩ እንደሆነ ምልከታ አደርጋለሁ ብሏል
አረጋውያን እነማን ናቸው? በአረጋውያን ላይ የሚደርስ ጥቃት ምን ማለት ነው? አረጋውያን ላይ የሚደርሱ የጥቃት አይነቶች ምን ምን ናቸው?
Older persons have the right to be protected from abuse and harmful traditional practice
አረጋውያን ከጥቃት እና ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የመጠበቅ መብት አላቸው
ውጤታማ እና ትርጉም ያለው የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎን ለማረጋገጥ የግምገማና የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት ቁልፍ ተግባራት ናቸው