አካል ጉዳተኞች በሚመለከቷቸው ሕጎች እና ፖሊሲዎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉበትን መድረኮች ትርጉም ባለው መልኩ ማመቻቸት የሁሉም ባለድርሻዎች ኃላፊነት ነው
የአካል ጉዳተኛ መንገደኞችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ፣ ተደራሽ እና አካታች ሊሆን ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለአካል ጉዳተኞች ያለው ተደራሽነት ላይ ያተኮረ ባለ 30 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ የተስተዋሉ መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ጉዳዮች፣ የአካል ጉዳተኛ መንገደኞች ተሞክሮ፣ ዝርዝር ምክረ ሐሳቦች እና ክትትሉ ከተከናወነ በኋላ የተስተዋሉ ለውጦች እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠውን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር የሰጠው የጽሑፍ ምላሽ ተካተዋል።...
በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) መሠረት የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ዕጩዎች ጥቆማ እስከ ታኅሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚቆይ ነው
የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች መከበር እና መጠበቅ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል
የሁሉንም የሰው ዘር አባላት በተፈጥሮ የተገኘ ክብር እንዲሁም እኩል እና የማይገፈፉ መብቶች ዕውቅና መስጠት በዓለም ላይ ለነጻነት፣ ፍትሕ እና ሰላም መሠረት ነው
Recognition of the inherent dignity and of the equal and inalienable rights of all members of the human family is the foundation of freedom, justice and peace in the world
States Parties shall take effective and appropriate measures, including through peer support, to enable persons with disabilities to attain and maintain maximum independence, full physical, mental, social and vocational ability, and full inclusion and participation in all aspects of life
አባል ሀገራት የእርስ በርስ ድጋፍን በመጠቀም ጭምር አካል ጉዳተኞች የላቀ ነጻነት፣ የተሟላ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ማኅበራዊና ሞያዊ ችሎታ እንዲሁም በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ውስጥ የተሟላ ተካታችነትና ተሳትፎ እንዲኖራቸው እና ይህንንም አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ውጤታማና ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳሉ
የአካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን መብቶች ማስጠበቅ፣ ደኅንነታቸውን ማረጋገጥ እና ለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶችም ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል