On Sunday, the government-appointed Ethiopian Human Rights Commission called on the federal government to find a “lasting solution” to the killing of civilians and protect them from such attacks
የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለተሻለ ዓለም!
ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን በምናስብበበት በዚህ ወር ውስጥ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ማሻገር በሴቶችና ሕፃናት ላይ ሰብአዊ መብቶች ጥሰት እያደረሰ በመሆኑ ምላሽ ለመስጠት የሚደረጉ ጥረቶችን ውጤታማ ለማድረግ በጋራ መስራት አስፈላጊነትን ማስታወስ ተገቢ ነው
ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ሰፊ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ በቅርቡ በአፋርና በአማራ ክልሎች የተካሄዱ ጦርነቶችን የተመለከተ አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
የሰብአዊ መብቶችን በማስከበር ረገድ ሚና ያላቸው የሰብአዊ መብቶች ተቋማት እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትም በሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ላይ መረጃ የመሰብሰብ፣ የክትትል ሥራዎች እና ጥሰቶችን የማጋለጥ ሥራዎች መስራት አለባቸው።
የሳምንቱ የሰብአዊ መብቶች ጽንሰ-ሀሳብ ፥ ከመጋቢት 5 እስከ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ያለው ሳምንት
የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት በሴቶች እና በወንዶች መካከል መድልዎ የሚከለክልና በሁሉም የሕይወት ዘርፎች እኩል መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፤ ሁሉም ሰዎች ያለምንም ልዩነት በሕግ ፊት እኩል እንደሆኑና እኩል የሕግ ጥበቃ ሊደረግላቸው የሚገባ መሆኑን የሚያመላክት መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች መርህ ነው፡፡
ዩኒሴፍ እ.ኤ.አ. በ2020 ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ 25 ሚሊዮን ልጃገረዶችና ሴቶች የሴት ልጅ ግርዛት የተፈጸመባቸው መሆኑን የሚጠቁም ሲሆን ይህ አሃዝ በምስራቅ እና በደቡብ አፍሪካ ከተመዘገበው ከፍተኛው መሆኑን መረጃው ይገልጻል፡፡
ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።
ኢሰመኮ በማቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ወቅት ሰብአዊ መብቶችን የሚከታተል መሆኑንና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለኮሚሽኑ የክትትል ተግባራት ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ለማስታወስ ይወዳል