የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 29 (5)
- በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል።
የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 34፣ አንቀጽ 16
- አባል ሀገራት የመንግሥት/የሕዝብ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ሰጪዎች በነጻነት ሥራቸውን ማከናወናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። በዚህ ረገድ፣ አባል ሀገራት ለእነዚህ ተቋማት ለተቋማዊ እና ለኤዲቶሪያል ነጻነታቸው ዋስትና ሊሰጡ ይገባል። መንግሥታት የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍም ይህንን ነጻነታቸውን የማይጋፋ መሆን አለበት።