Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

አዲስ አበባ፡ የከተማ አስተዳደሩ ባለሦስት እና አራት እግር (ባጃጅ) አነስተኛ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ላይ ያስቀመጠውን ሙሉ እገዳ በማንሳት ለችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያመቻች ይገባል

March 16, 2023August 28, 2023 Press Release

በጠቅላላ ከተማው ላልተወሰነ ጊዜ ገደብ መጣሉ ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የተደረገላቸው መብቶች አደጋ ላይ የጣለ እርምጃ ነው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎትን ከየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይሰጥ እገዳ መጣሉና እገዳውም ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ እስከሆነበት ጊዜ አለመነሳቱ በተለያዩ ሰብአዊ መብቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ገደብ የሚጥል እርምጃ በመሆኑ እጅግ አሳሳቢነቱን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ እገዳውን አስመልክቶ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ “የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል የአሠራር ማሻሻያ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑንና፣ የማሻሻያ ሥራው ተሠርቶ እስኪጠናቀቅ እና የባጃጅ ትራንስፖርት የአገልግሎት አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ” በሚል ምክንያት ከየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እገዳ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል። ኮሚሽኑ ይህንን እገዳ ተከትሎ የደረሱትን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችን አነጋግሯል። ኃላፊዎቹ በከተማዋ ወደ 10 ሺህ የሚገመቱ “የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ፈቃድ ያልተሰጣቸው መሆኑን፣ እንደ አንድ አገልግሎት ሰጪ በከተማዋ አሠራር ሥርዓት ያልተዘረጋላቸው መሆኑን፣ እንዲሁም ሌሎችም ተዛማጅ ችግሮች” መኖራቸውን ይገልጻሉ። በተጨማሪም “ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ከዋና መንገዶች ውጪ ባሉ ውስጥ ለውስጥ መንገዶች እስከ ሁለት ኪሎ ሜትር ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ማስተካከያ እየተወሰደ መቆየቱን”፤ ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች ባጃጆቹ ከተቀመጠላቸው የእንቅስቃሴ አካባቢ ውጪ በዋና መንገዶች ላይ ሲሠሩ በመታየታቸው እና የከተማው የትራንስፖርት ፍሰት ላይ ጫና መፍጠሩን ይናገራሉ። እገዳው በሁሉም ቦታ የተደረገው “ልዩነት እና መድሎ ላለመፍጠር” እንደሆነና የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች በማኅበር ተደራጅተው የሚሠሩ በመሆኑ አሠራሩን ስለማሻሻል ከማኅበራቱ ጋር የተደረጉ ውይይቶች እንደነበሩ ያስረዳሉ።

በሌላ በኩል እገዳው በተጣለበት በየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. “በተቃውሞ መንገድ የዘጉ የጋርመንት አካባቢ ባጃጅ ሹፌሮች” ታስረው የነበረና ወደ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስትና መለቀቃቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል እገዳው በከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ መሆኑ የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎቹንና ቤተሰባቸውን ብቻ ሳይሆን፣ እጅግ በርካታ ተጠቃሚዎችንም ችግር ላይ እንደጣለ መረዳት ተችሏል።

መንግሥት ሰዎች ሥራቸውን እና የመረጡትን መተዳደሪያ ያለአግባብ እንዳያጡ ማድረግን ጨምሮ የመረጡትን እና የተቀበሉትን ሥራ እንዲሠሩ የማስቻል ኃላፊነት አለበት። በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 41(1) መሠረት “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራት እና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመሥራት መብት” ያለው ሲሆን በንዑስ-አንቀጽ 2 እንደተመለከተው መተዳደሪያውን፣ ሥራውን እና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው። ይህ መተዳደሪያን የመምረጥ/በመረጡት ሥራ የመሰማራት መብት (the right to choose one’s livelihood/work) ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶችም የተረጋገጠ መብት ነው፡፡ በተጨማሪም የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 41(6) እንደሚደነግገው መንግሥት ለሥራ አጦች እና ለችግረኞች ሥራ ለመፍጠር የሚያስችል ፖሊሲ የመከተል፤ በሚያካሂደው የሥራ ዘርፍ ውስጥ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሥራ ፕሮግራሞችን የማውጣት እና ፕሮጀክቶችን የመቅረጽ ግዴታ አለበት። የዚሁ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ 7 ደግሞ መንግሥት ዜጎች ጠቃሚ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት ይደነግጋል። ሕገ-መንግሥቱ በምዕራፍ አስር ከተካተቱት የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆችና ዓላማዎች መካከል ስለኢኮኖሚ ነክ ዓላማዎች በሚደነግገው በአንቀጽ 89(2) ላይ መንግሥት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማድረግ ሁኔታዎች የማመቻቸት ግዴታ እንዳለበት ይገልጻል። የዚሁ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ 8 ደግሞ መንግሥት የሠራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደኅንነት እና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር እንዳለበት ይገልጻል።

ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ በተደረገላቸው በእነዚህ ሰብአዊ መብቶች ላይ ገደብ በሚጣልበት ጊዜ መብቶችን ለመገደብ የሚያስችል የሕግ መሠረት መኖር (legality)፣ የገደብ እርምጃ የሚወሰደው ቅቡል ዓላማን ለማሳካት ሲሆን (legitimacy)፣ ዓላማውን ለማሳካት የገደቡ አስፈላጊነት (necessity) እና የገደቡን ተመጣጣኝነት (proportionality) መርሆች ሊከተል ይገባል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከእነዚህ ሰብአዊ መብቶች መርሆች አንጻር በባጃጅ የትራንስፖርት ሥራ የተፈጠሩትን ችግሮች በተገቢው ሕጋዊ እርምጃዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በማስተዳደር እና ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ ማድረግ ሲገባ፣ በጠቅላላ ከተማው ላልተወሰነ ጊዜ ገደብ መጣሉ ከላይ የተገለጹትን ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የተደረገላቸው መብቶችን አደጋ ላይ የጣለ እርምጃ ነው፡፡ በተለይም በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንን እንዲሁም ሴቶች እና ሕፃናትን ታሳቢ በማድረግ እገዳውን ማንሳትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

Related posts

February 15, 2023August 28, 2023 EHRC Quote
ኢሰመኮ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተደረጉ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ተከታዮች እና የተለያዩ ሚዲያ አባላት እስር በእጅጉ እንደሚያሳስብ ገለጸ
October 6, 2022October 6, 2022 Press Release
ጋምቤላ ክልል፡ በጋምቤላ ከተማ በብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋም እና ሠራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በክልሉ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ምልከታ የሚጥል በመሆኑ የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ሊያስቆሙ ይገባል
February 6, 2023August 28, 2023 Press Release
በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል የሚያደርግ የባለሙያዎች ቡድን ኢሰመኮ አሰማራ
February 15, 2023February 15, 2023 Press Release
ኦሮሚያ ክልል፡ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ኢላማ በማድረግ የተፈጸመው ጥቃት በክልሉ በቀጠለው ግጭት ምክንያት የሲቪል ሰዎች ደኅንነት የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.