Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ከትግራይ ክልልና ከአዋሳኝ የአማራ ክልል አካባቢዎች ተፈናቅለው በአዋሽ ሰባት የተያዙ ሰዎች የመንቀሳቀስ መብት በአፋጣኝ ሊከበር ይገባል

September 9, 2022October 20, 2023 Press Release

ሰዎቹ ከሌሎች የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች በተለየ መልኩ ከሕግ አግባብ ውጪ እና የመንቀሳቀስ መብታቸው ተነፍጎ፣ የሰብአዊ ድጋፍ በበቂ ሁኔታ ሳይቀርብላቸው በጃሬ መጠለያ ጣቢያ ለበርካታ ወራት ተይዘው ቆይተዋል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ከጃሬ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ወደ አዋሽ ሰባት የፌዴራል ፖሊስ ማሰልጠኛ እንዲዘዋወሩ የተደረጉ ከትግራይ ክልልና ክልሉን ከሚያዋስኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አፋጣኝ ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑን አስታወቀ። ኮሚሽኑ በጃሬ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ ተፈናቃዮችን ሁኔታ ከግንቦት ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ መጠለያ ጣቢያው በአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች የሆኑ እና ከመሀል ትግራይ ከተሞች መቀሌ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ ሽሬ እና አካባቢው ተፈናቅለው የመጡ በወቅቱ 2,800 የሚሆኑ ሰዎች የሚገኙበት ነበር።

ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገበት ወቅት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች ወደ ጃሬ መጠለያ ጣቢያ እንዲገቡ ሲደረግ “የጸጥታ ሥጋት ሁኔታ እስከሚጣራ ድረስ ነው የምትቆዩት” በሚል የተነገራቸው መሆኑን የገለጹ ቢሆንም፤ ማጣራት ሳይደረግ ለረዥም ወራት በቂ የሰብአዊ ድጋፍ በሌለበት እና ከእስራት ጋር በሚመሳሰል ነገር ግን ከቤተሰብ ለመገናኘት በማይቻልበት እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲቆዩ መደረጋቸውን ተመልክቷል።

ለተፈናቃዮች የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሰብአዊ ድጋፎችን ለማቅረብ ጥረት ሲያደርግ የቆየው የፌዴራል አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች በአካባቢው የጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎች በደረሰባቸው ተጽዕኖ ሥራቸውን ለማቋረጥ መገደዳቸውን ለመረዳት ተችሏል። በተጨማሪም በወቅቱ መጠለያ ጣቢያው በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ሥር የነበረ በመሆኑ አጋር የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ድጋፍ ለማድረግ ተነሳሽነት ባለማሳየታቸው ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እጥረት መዳረጋቸውን፣ እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያው የሕክምና አገልግሎት ያልነበረ በመሆኑ ተፈናቃዮች የሕክምና እርዳታ ለማግኘት ጭምር በመጠለያ ጣቢያው የጸጥታ አካላት የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጥ ፍቃድ ብቻ እና በክፍያ በሚደረግ እጀባ ለመንቀሳቀስ ተገድደው የነበረ መሆኑን ኮሚሽኑ ባከናወነው ክትትል አረጋግጧል።

ኢሰመኮ በጃሬ የመጠለያ ጣቢያ የነበረውን አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በክትትል ከለየ በኋላ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ተቋማት የሁኔታውን አሳሳቢነት በመግለጽ ተፈናቃዮቹ በሕግ አግባብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ባለመሆናቸው የመንቀሳቀስ መብታቸው ሊረጋገጥላቸው የሚገባ መሆኑን፤ ከመካከላቸው የጸጥታ ሥጋት ናቸው በሚል በምክንያታዊነት የሚጠረጠሩ ሰዎች ካሉ የመለየት፣ የመመርመር እና በሕግ አግባብ ተጠያቂ የማድረግ ሥራው ግልጽ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ እንዲፈጸም ሲጠይቅ ቆይቷል። እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ሰብአዊ ድጋፎች (በቂ ምግብ፣ መጠለያ፣ ንጹሕ የመጠጥ እና የመገልገያ ውሃ፣ አስፈላጊ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና ሌሎች ድጋፎች ጨምሮ)፤ እና የሕክምና አገልግሎቶች ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ተፈናቃዮችን ፍላጎቶች ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲቀርቡ የሚያሳስቡ የቃልና የጽሑፍ መልእክቶችና ምክረ ሃሳቦች ያስተላለፈ ሲሆን፣ ተፈጻሚነቱን ለማረጋገጥ ከተቋማቱ የበላይ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር ተደጋጋሚ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

ሆኖም በተፈናቃዮች ሁኔታ ላይ ተጨባጭ መሻሻል ሳይታይ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በቅርቡ በድጋሚ መቀስቀሱን ተከትሎ በጃሬ መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ተፈናቃዮች አዋሽ ሰባት ወደሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲዘዋወሩ መደረጉን ኮሚሽኑ አረጋግጧል። ኮሚሽኑ ተፈናቃዮችን በመጎብኘት አሁን የሚገኙበትን ሁኔታ ክትትል የማድረግ ጥረቱ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በጸጥታ አካላቱ ጉብኝት አለመፍቀድ ምክንያት ሳይሳካ የቀረ ሲሆን፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች የኮሚሽኑን ጉብኝት በአስቸኳይ እንደሚያመቻቹ አሁንም ይጠበቃል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንደገለጹት ለሕዝብ ጸጥታ፣ ደኅንነት እና ጤና ወይም የተፈናቃዮችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ሲባል በተፈናቃዮች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ሊጣል የሚችልበት ሁኔታ ቢኖርም፤ የዚህ አይነቱ ገደብ የአስፈላጊነት፣ ምክንያታዊነት እና ተመጣጣኝነት መርሆችን በጥብቅ በተከተለ መንገድ ሊከናወን የሚገባው መሆኑን አሳስበው “በአዋሽ ሰባት የፌዴራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች የመጡባቸውን የትግራይ ክልል አካባቢዎች ብቻ መሰረት በማድረግ ለተራዘመ ጊዜ የመንቀሳቀስ ነጻነታቸውን ተነፍገው እንዲቆዩ መደረጉ የአስፈላጊነት፣ ምክንያታዊነት እና የተመጣጣኝነት መርሆዎችን የሚቃረን ነው” ብለዋል።

ስለሆነም ተፈናቃዮቹ በሕግ አግባብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ባለመሆናቸው በመካከላቸው የጸጥታ ሥጋት ናቸው በሚል በምክንያታዊነት የሚጠረጠሩ ሰዎች ካሉ በመለየት፣ በመመርመር እና በሕግ አግባብ ተጠያቂ የማድረግ ሥራው ግልጽ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ በአፋጣኝ እንዲከናወን ኮሚሽኑ ያሳስባል። ሌሎች ተፈናቃዮች ሁሉ የመንቀሳቀስ መብታቸው በአስቸኳይ ሊረጋገጥላቸው፤ በመጠለያ ጣቢያዎች መቆየት የሚያስፈልጋቸው ተፈናቃዮችም የሲቪል ባሕርይ ወዳለው ጣቢያ ሊዘዋወሩ፤ እንዲሁም አስፈላጊ እና በቂ የሆኑ የሰብአዊ ድጋፎች እና አገልግሎቶች (በቂ ምግብ፣ መጠለያ፣ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ፣ አስፈላጊ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ ሕክምና ወዘተ) ሊቀርቡላቸው በሚችል ሁኔታ ውስጥ ሊሆን እንደሚገባ ኢሰመኮ በድጋሚ ያሳስባል።

Related posts

October 2, 2023October 4, 2023 Press Release
በሶማሊ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ ላይ በክልሎቹ የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት ተገቢ የሆነ ምርመራ በማድረግ ለተጎጂዎች ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል
February 22, 2023February 22, 2023 Press Release
አፋር ክልል: የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ተመላሾች በዘላቂነት እንዳይቋቋሙ ተግዳሮት ከሆነው የኢኮኖሚ እና የንግድ እንቅስቃሴ ገደብ ጋር የተገናኙ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል
June 1, 2023June 1, 2023 Press Release
በሸገር ከተማ ከመስጊዶች መፍረስ ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችን እና የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ
June 7, 2021February 12, 2023 Report
ብዛት ያላቸው ተፈናቃዮች ከግንቦት 16 ቀን 2013 ጀምሮ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘዋል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.