ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 18
- ሁሉም ሰው የማሰብ፣ የኅሊና እና የሃይማኖት ነጻነት መብት አለው፡፡ ይህ መብት ሃይማኖትን ወይም እምነትን የመለወጥ፣ እንዲሁም ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በኅብረት፣ በግል ወይም በአደባባይ ሃይማኖትን ወይም እምነትን የማስተማር፣ የመተግበር፣ የማምለክ እና የመከተል ነጻነትን ይጨምራል።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 27(5)
- ሃይማኖትንና እምነትን የመግለጽ መብት ሊገደብ የሚችለው የሕዝብን ደኅንነት፣ ሰላምን፣ ጤናን፣ ትምህርትን፣ የሕዝብን ሞራል፣ የሌሎች ሰዎችን መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ለማስጠበቅ እና መንግሥት ከሃይማኖት ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ሕጎች ይሆናል።