Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

የመንግሥት በጀት አመዳደብ ከሰብአዊ መብቶች አኳያ

January 11, 2024January 11, 2024 Explainer

በበጀት አመዳደብ ሂደት ሰብአዊ መብቶች ተኮር መሆን ማለት ሀብትን የሰው ልጆችን ባስቀደመ መልኩ ወይም ሰዎችን ማዕከል በሚያደርግ መንገድ መመደብ ነው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

ሰብአዊ መብቶች ተኮር የበጀት አመዳደብ (Human Rights–Based Budgeting) ምን ማለት ነው?

መንግሥት በሕጎች፣ ፖሊሲዎች፣ ዕቅዶች እና ፕሮግራሞች የተቀረጹ ሊያሳካ የሚፈልጋቸውን ዓላማዎች ከሚያስፈጽምበት አንዱ እና ዋነኛው መንገድ በጀት ነው።

በበጀት አመዳደብ ሂደት ሰብአዊ መብቶች ተኮር መሆን ማለት ሀብትን የሰው ልጆችን ባስቀደመ መልኩ ወይም ሰዎችን ማዕከል በሚያደርግ መንገድ መመደብ ነው። ይህ ዐይነቱ የበጀት አመዳደብ ሂደት ገንዘብ የሚመነጭበት፣ የሚከፋፈልበት እና ሥራ ላይ የሚውልበት ሂደት በሰዎች የሰብአዊ መብቶች ላይ የሚኖረውን አንድምታ ከግምት ውስጥ ማስገባትን ይጠይቃል።

በተለይም የበጀት ውሳኔዎች የሰብአዊ መብቶች መርሖችን ሊያንጸባርቁ፣ እንዲሁም በጀት የማዘጋጀት፣ የማጽደቅ፣ የመፈጸም እና በጀቱን ኦዲት የማድረግ ሂደቱ በሰብአዊ መብቶች መርሖች ሊመራ ያስፈልጋል። የበጀት አወሳሰን ሂደቱ ዴሞክራሲያዊ እና አሳታፊ መሆኑን ማረጋገጥ የመብት ተኮር በጀት አመዳደብ ወሳኝ ገጽታ ነው። ስለሆነም መብት ተኮር የበጀት አመዳደብ የዚህ ሁሉ ሂደት አካል ሊሆን ይገባል። በተለይም የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ፖሊሲ በመቅረጽ እና ዕቅድ በማውጣት የሚሠሩ አካላት ከበጀት አመዳደብ ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር በቅርበት መሥራት ይጠበቅባቸዋል።

መንግሥታት ገንዘብ የሚያመነጩበት፣ የሚያከፋፍሉበት እና ሥራ ላይ የሚያውሉበት ሂደት የመንግሥት ሰብአዊ መብቶችን የማክበር፣ የማስከበር እና የማሟላት ኃላፊነት ላይ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ስለሆነም፡-

  1. የበጀት አመዳደብ ሂደት መንግሥት ለመብቶች ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይበት አንዱ መንገድ በመሆኑ የሰብአዊ መብቶች መርሖች በበጀት አመዳደብ ሂደቱ ላይ ሊንጸባረቁ ይገባል፣
  2. መብት ተኮር የበጀት አመዳደብ፣ በጀት በሚመደብበት ጊዜ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን እንዳለበት የሚያስገነዝብ ሲሆን፣ ሰብአዊ መብቶች ተኮር የበጀት አመዳደብ ሰፊ የሆነ የፖሊሲ ሂደት ነው።

መብት ተኮር የበጀት አመዳደብን ለመከተል የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎችን መለየት፣ በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ ቡድኖች የሚገጥሟቸውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ምን እንደሆኑ መተንተን፣ ለምሳሌ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የትምህርት፣ የጤና እና የመጠለያ ሁኔታዎች ምን እንደሚመስሉ መገንዘብ፣ እነዚህን የተለዩ የመብት ጥሰቶች ለማረም የሚበጅ ፖሊሲ መቅረጽ፣ የተቀረጸው ፖሊሲ ሥራ ላይ እንዲውል የሚያስችል በቂ በጀት መመደብ፣ የተመደበው በጀት ለታሰበለት ዓላማ መዋሉን መቆጣጠር፣ እንዲሁም ፖሊሲው መፈጸሙን እና ያመጣውን ውጤት (impact) መገምገም አስፈላጊ ነው።

ሰብአዊ መብቶች ተኮር በጀት አመዳደብን በተመለከተ ያሉ የሕግ ድንጋጌዎች ምንድን ናቸው?

በፌዴራል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 9(4) መሠረት ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች የሀገሪቱ የሕግ አካል ናቸው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ በምዕራፍ 3 ስር የተካተቱትን የሰብአዊ መብቶችን የማሟላት፣ የማክበር እና የማስከበር ኃላፊነት በየደረጃው ባሉ የፌዴራል እና የክልል የመንግሥት አካላት ላይ ይጥላል። ግለሰቦች እና ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላትም ሰብአዊ መብቶችን የማክበር እና የማስከበር ኃላፊነት አለባቸው።

በተጨማሪም በሕገ-መንግሥቱ የተዘረዘሩ የሰብአዊ መብቶች ከዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች አንጻር መተርጎም እንዳለባቸው ሕገ መንግሥቱ በግልጽ በመደንገግ የሰብአዊ መብቶችን ሕገ መንግሥታዊና ዓለም አቀፋዊ የሕግ መሠረት ከፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች፣ ስምምነቱን በተቀበሉ አባል ሀገራት ላይ ሁሉ የተለያዩ ኃላፊነቶችን እና ግዴታዎችን ይጥላሉ። ከእነዚህ ግዴታዎች ውስጥ አንዱ በእነዚህ ስምምነቶች ውስጥ የተዘረዘሩ የሰብአዊ መብቶችን ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ ተገቢውን ሀብት ወይም በጀት በመመደብ መብቶቹ እንዲሟሉ፣ እንዲጠበቁና ተፈጻሚ እንዲሆኑ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው።

ከበጀት አመዳደብ ጋር በተገናኘ ሀብት (resource) የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን ጨምሮ ሁሉንም መብቶች ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ያለው ነው፡፡ ዓለም አቀፉን የሕጻናት መብቶች ስምምነትን አፈጻጸም የሚከታተለው ኮሚቴ ሀብት የሚለው ፅንሰ-ሐሳብ ሰፊ እንደሆነና  የሰው ሀብትን (human resource)፣ የቴክኒክ ሀብትን (technical resource)፣ ተቋማዊ ሀብትን (organizational resource)፣ የተፈጥሮ ሀብትን (natural resource) እና የመረጃ ሀብትን (information resources) እንደሚያካትት ያስረዳል።

የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን በአንቀጽ 2(1) ስር ማንኛውም የቃልኪዳኑ አባል ሀገር በግሉ እና በተለይ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክኒካዊ ድጋፍ በታከለበት ዓለም አቀፍ እርዳታ እና ትብብር አማካኝነት በእጁ የሚገኙትን ሀብቶች አሟጦ በመጠቀም በቃልኪዳኑ ዕውቅና ያገኙት መብቶች በሂደት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ ሕግ ማውጣትን ጨምሮ ማናቸውንም ተገቢ እርምጃዎች መውሰድ እንዳለበት ይደነግጋል። በዚህም መሠረት ሀብት ማለት በሀገር ውስጥ የሚገኘውን ብቻ ሳይሆን ከላይ እንደተጠቀሰው ከዓለም አቀፍ ትብብር እና እርዳታ የሚገኘውንም ሀብት ጭምር ያካትታል። በተጨማሪም የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶችን በተመለከተ የሚያብራራው መመሪያ (Maastricht Guidelines) አንድ ሀገር ለሰብአዊ መብቶች መከበር እንዲረዳ  ያለውን ሀብት አሟጦ መመደብ ካልቻለ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን  ሊያስከትል እንደሚችል ይገልጻል።

ስለሆነም  ከመንግሥት የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎች ጋር የሚጣጣም በጀት ለመመደብ በእጅ ላይ ያለውን ሀብት ውጤታማ እና ከአድሎ በጸዳ መልኩ መጠቀም ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ሀብትን ለማመንጨት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። በአጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ተኮር የበጀት አመዳደብ የሰብአዊ መብቶችን ለማረጋገጥ እንዲያስችል መንግሥታት የሚችሉትን ዐቅም ሁሉ ተጠቅመው በሀገር ውስጥ ሀብትን ማመንጨት (mobilize resources) እና ከውጭ የሚገኝ ሀብትንም ማሰባሰብ ይኖርባቸዋል።

የመንግሥት ሀብትን የማመንጨት እና የተገኘውን ሀብት ሥራ ላይ የማዋል ሂደት ውጤታማ (efficient) መሆን ይኖርበታል። በተጨማሪም ሙስናን አለመከላከል  ሀብትን በአግባቡ የሰብአዊ መብቶችን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ ሥራ ላይ የማዋል ከሰብአዊ መብት ስምምነቶች የሚመነጭ ግዴታን የሚጥስ ነው። በዚህ ረገድ አባል ሀገራት ሙስናን ለመከላከል በሕዝብ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ግልጸኝነትንና ተጠያቂነትን ሊያሰፍኑ እንደሚገባ ሙስናን ለመከላከል እና ለመዋጋት የተደረገ የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት ይገልጻል።

በተጨማሪም መንግሥታት መብቶችን ወደኋላ ሊወስድ የሚችል እርምጃዎችን (retrogressive measures) ከመውሰድ መቆጠብ ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ከዚህ ቀደም ይመደብ የነበረው በጀት ላይ ቅናሽ የማድረግ እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት በእጃቸው ላይ ያለውን ሀብት አሟጠው መጠቀማቸውን ማስረዳት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ያለው ሀብት የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን ለማረጋገጥ በቂ ካልሆነ  ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ትብብር እና ድጋፍ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

መብቶች ተኮር የበጀት አመዳደብ ሊከተላቸው የሚገቡ መርሖች ምንድን ናቸው?

ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ የበጀት አመዳደብ ሲባል በአጠቃላይ የበጀት ሂደቱ በሰብአዊ መብቶች መርሖች ሊመራ ይገባል ማለት ነው። ይህም  የበጀት አመዳደብ ሂደቱ አሳታፊ እና የመረጃ ተደራሽነትን ከግምት ያስገባ፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት፣ ውጤታማ መፍትሔ ሊሰጡ የሚችሉ አካላት ያሉት፣ ከአድሎ የጸዳ፣ ሰዎችን በማብቃት ላይ የተመሠረተ እና ሕጋዊ ሊሆን ይገባል።

የአሳታፊነት መርሕ (Principle of Participation)

ይህ መርሕ ሁሉም ሰዎች በበጀት ሂደቱ ውስጥ ንቁ እና ትርጉም ያለው ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው የሚያብራራ መርሕ ነው። ሁሉም ሰው የሰብአዊ መብቶቹን ሊነካ በሚችል ማንኛውም የውሳኔ ሂደት ተሳታፊ ሊሆን ይገባዋል። ግለሰቦች የነቃ፣ ትርጉም ያለው እና ነጻ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ ተደራሽ የሆነ የመረጃ እና የተግባቦት ሥርዓት መፍጠር  አስፈላጊ ነው። ሁሉም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ በበጀት ሂደቱ እንዲሳተፉ ማድረግን ያካትታል።

የተጠያቂነት እና ግልጽነት መርሕ (Principle of Accountability and Transparency)

ይህ መርሕ የበጀት አመዳደብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሆኑ የመንግሥት አካላት በጀቱን በተመለከተ ተጠያቂነት እንዳለባቸው የሚገልጽ ነው። ምክንያቱም ሰብአዊ መብቶችን የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታ የተጣለበት አካል ስለሆነ እና ግዴታን አለመወጣት ደግሞ ተጠያቂ ስለሚያደርግ ነው። ስለሆነም በጀቱን የተመለከተ በቂ መረጃ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እና ግልጽነት የተሞላበት የበጀት አመዳደብ ሥርዓት ሊኖር ይገባል። ይህ ሳይሆን ሲቀር የሚመለከታቸው አካላት ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን ለማስፈን ተገቢነት ላለው የሕግ አካል ጉዳያቸውን በማቅረብ ተገቢውን  ሕጋዊ መፍትሔ የማግኘት መብት አላቸው። ተጠያቂነትን ለማስፈን የተለያዩ እርምጃዎች መወሰድ ያለባቸው ሲሆን፣ ለምሳሌ  ግልጽነት የተሞላበት የበጀት ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ እና የበጀት ትንተና ዐቅምን ማሳደግ ነው። የሰብአዊ መብቶችን ተግባራዊነት ለመከታተል የሚረዱ መረጃዎች ተደራሽ እንዲሆኑ መወትወት፣ የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት እንዲኖር ማበረታታት እና ባለመብቶች መብቶቻቸውን መጠየቅ እንዲችሉ ዐቅም መገንባትን ይጨምራል፡፡

እኩልነት እና ከአድሎአዊ ልዩነት የመጠበቅ መርሕ(Equality and Non-Discrimination)

ይህ መርሕ ሁሉም ሰዎች ያለምንም ልዩነት እና አድሎአዊነት ሁሉም የሰብአዊ መብቶች ለሁሉም በእኩልነት ተፈጻሚ መሆን እንዳለባቸው ይገልጻል። በተጨማሪም በበጀት አመዳደብ ሂደት፣ ለተገለሉና ተጋላጭ  ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሰብአዊ መብቶቻቸውን ከሌሎች እኩል መጠቀም እንዲችሉ ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ያስገነዝባል።

የማብቃት መርሕ (Empowerment)

ማብቃት ወይም የሰዎችን ዐቅም ማጎልበት ሌላው መርሕ ነው። ማንኛውም ሰው በዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ ሕጎች ዕውቅና የተሰጣቸውን የሰብአዊ መብቶች እና ነጻነቶች እንዲከበሩለት የመጠየቅ እና መብቶቹንም የመጠቀም መብት አለው። ስለሆነም ግለሰቦች እና ማኅበረሰቡ መብቶቻቸውን ማወቅ እንዲሁም መብቶቻቸው ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ፖሊሲዎች እና የበጀት አመዳደብ ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በመሆኑም፣ እነዚህ የኅብረተሰብ ክፍሎች መብቶቻቸውን እንዲገነዘቡ እና በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋል እንዲችሉ አስፈላጊውን ዐቅም መፍጠር ወይም ማብቃት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የሕጋዊነት መርሕ (Legality)

ይህ መርሕ የበጀት አመዳደብ ሂደት ሕጋዊነት መከተል እንዳለበት ያሳስባል። በዚህም የበጀት አመዳደብ ሂደቱ በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሕጎች ዕውቅና የተሰጣቸውን መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶችን መሠረት ያደረገ፣ አግባብነት ያላቸውን የአገሪቱን ሕጎች ያከበረ፣ እንዲሁም ከሰብአዊ መብቶች መርሖች ጋር የተጣጣመ የበጀት አመዳደብ ሊኖር ይገባል።

Related posts

September 3, 2021August 28, 2023 Press Release
የሰብአዊ መብቶች ትምህርት በመደበኛ ትምህርት ሥርአተ-ትምህርት ውስጥ በአግባቡ ሊካተት ይገባል
October 30, 2021August 28, 2023 Press Release
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሰብአዊ መብት ዙሪያ ከወጣት ማህበራት ለተወጣጡ ተሳታፊዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ
June 20, 2021February 12, 2023 Press Release
ኢሰመኮ በምርጫው እለት የሰብአዊ መብቶች ክትትል ለማድረግ ባለሙያዎች ማሰማራቱን አስታወቀ
June 18, 2021February 12, 2023 Press Release
በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብአዊ መብቶችን አክብረው መንቀሳቀስ አለበቸው

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.