የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 9(2)
- ማንኛውም ሰው በሚያዝበት ጊዜ የተያዘባቸውን ምክንያቶችና የቀረቡበትን ክሶች ምንነት ወዲያውኑ የማወቅ መብት አለው፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 19(2 እና 3)
- የተያዙ ሰዎች ያለመናገር መብት አላቸው፤ የሚሰጡት ማንኛውም ቃል ፍርድ ቤት በማስረጃነት ሊቀርብባቸው እንደሚችል መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንደተያዙ ወዲያውኑ እንዲያውቁት መብት አላቸው።
- የተያዙ ሰዎች በ 48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው። ይህም ጊዜ ሰዎቹ ከተያዙበት ቦታ ወደ ፍርድ ቤት ለመምጣት አግባብ ባለው ግምት የሚጠይቀውን ጊዜ አይጨምርም።