የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 9 (1) (4)፣ 10 (1)

  • ማንኛውም ሰው በዘፈቀደ ሊያዝ ወይም ሊታሰር አይችልም። ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ምክንያትና ሥርዓት ውጭ ነጻነቱን አይነፈግም፡፡
  • በመያዙ ወይም በመታሰሩ ምክንያት ነጻነቱን የተነፈገ ማንኛውም ሰው ፍርድ ቤቱ ሳይዘገይ ስለእስራቱ ሕጋዊነት እንዲወስንለትና ያለአግባብ መታሰሩን ካረጋገጠም በነጻ እንዲለቀቅ እንዲያዝለት ጉዳዩን ለፍርድ ቤት የማቅረብ መብት አለው፡፡
  • ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አያያዝ ሊደረግላቸውና በተፈጥሮ የተጎናጸፉት ሰብአዊ ክብር ሊጠበቅላቸው ይገባል፡፡